article stringlengths 137 2.14k | headline stringlengths 6 506 | language stringclasses 1 value | split stringclasses 3 values | template stringclasses 2 values | dataset stringclasses 1 value | config stringclasses 1 value | length int64 46 504 | category stringclasses 1 value | source_dataset stringclasses 1 value |
|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ።
የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል።
በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል።
ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል።
የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል።
በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መንገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል።
እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ።
ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው።
ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ።
ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል።
ኦክስጅንና ኦዞን
በሌላ መልኩ "አቶሚክ ኦክስጅንን" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል።
ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው።
ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም።
መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ "የኦዞን" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው።
በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል።
አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል።
ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል።
ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም።
'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር '
በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው።
ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል።
ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ... | ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት? | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 386 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በእንግሊዝ የሁለት ዓመቱ ታዳጊ በተፈጠረ የህክምና ስህተት መከነ\nህፃኑ ያለቦታው የተገኘ የዘር ፍሬውን ለማዛወር ወደ ብሪስቶል ሮያል የህፃናት ሆስፒታል የተላከው በዚህ ሳምንት መጀመርያ ነበር።
• ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ
• ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ የሚመጡ የሙያ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
• የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ጊታር የተጫወተው ግለሰብ
የህፃኑ አንዱ የዘር ፍሬ ጤናማ የነበረ ሲሆን አንደኛው ግን ያለቦታው ሆኖ ነበር የተወለደው። የህፃኑ አባት እንደሚሉት ይህንኑ ለማስተካከል በተደረገ ቀዶ ሕክምና ባጋጠመ ስህተት ጤናማውም ዘር እንዳያመነጭ ሆኗል።
የህፃኑን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ስማቸው ያልተጠቀሰው አባት የህፃኑ የዘር ፍሬ ያለ ቦታው እንደነበር ያወቁት በአጋጣሚ በተደረገ ቀላል ምርመራ ነበር።
ከዚያም ባለፈው ሰኞ ህፃኑ ለተሻለ ህክምና ወደ ብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ተልኮ ቀዶ ሕክምና ሊደረግለት ቀጠሮ እንደተያዘለት ይናገራሉ።
ወላጆቹ እንደሚሉት ቀዶ ጥገናው በጣም ቀላልና ለአደጋ የሚያጋልጠው አልነበረም፤ በ30 ደቂቃ እንደሚጠናቀቅም ያውቁ ነበር።
" ጠበቅን... ጠበቅን... ከ2 ሰዓት በላይ ከቆየን በኋላ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጂ፣ ሐኪሙና አማካሪው ወደ እኛ መጡ፤ ያኔ አንዳች መጥፎ ዜና እንዳለ ተረዳን" ይላሉ።
"በድንጋጤ ተብረከረኩ፤ "ወደ ቢሮ ተጠርተው ሁኔታዎች እንደታሰበው እንዳልሆነና ቀዶ ህክምናው ውጤታማ እንዳልነበር ተነገራቸው።
ህፃኑ የዘር ፍሬ ማመንጨት አይችልም የሚለው መርዶም ተነገራቸው።
" በጣም የሚያስጨንቅ ነው ፤ በጣም አስቀያሚ አጋጣሚ ነበር፤ ለቀላል ቀዶ ህክምና ሁሉንም ነገር አመከኑት " ሲሉ አባቱ ሃዘናቸውን ይገልፃሉ።
የልጃቸው የወደፊት ህይወትም በማይታመንና በሚያሳዝን መልኩ መለወጡን ይናገራሉ።
የህፃኑ እናት በበኩላቸው ሐኪሞቹ የሰሩት ስህተት በጣም ዘግናኝ ነው ብለዋል። "ልቤን ሰብረውታል፤ የእርሱንም የወደፊት ሕይወት አጨልመውታል" ሲሉ ልባቸው አንደተሰበረ ተናግረዋል።
" የተሰማኝን መግለፅ አልችልም ፤ምንም ቃላት የለኝም ፤ እንባም ቢሆን.... የሆነ ተአምር እንዲፈጠር ነው ተስፋ ያደረግነው፤ በቃ ያለን ተስፋ ይሄው ነው" ብለዋል።
ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ ላይ የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ እንደገለፁት ሰራተኞቹ ምን እንደተፈጠረ ባወቁ ጊዜ ወላጆቹን አስጠርቶ ይቅርታ ጠይቋል።
ሁኔታውን ለማጣራት ምርመራ መጀመሩን ገልፀው እየተከታተሉ ለቤተሰቦቹ እንደሚያስታውቁም ገልፀዋል።
በኤን ኤች ኤስ ሪፖርት ከ100 ህፃናት አንዱ ህክምና ካላደረገ በስተቀር ያለቦታው ከተቀመጠ የዘር ፍሬ ጋር ይኖራል።
| የሁለት ዓመቱ ህፃን የዘር ፍሬውን ለማስተካከል በተደረገ ህክምና ወቅት ባጋጠመ ስህተት መምከኑን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል። | amh_Ethi | test | tldr | GEM/xlsum | amharic | 295 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
አቶ አብዲ ድንገታ
ይህ ቴሌሜዲስን ተብሎ ይጠራል። ለመሆኑ በእኛ አገር ይህ የአማካሪዎች ሕክምና እንዴት ውጤታማ ሊሆን ይችላል?
የሰመመን ሕክምና ባለሙያና የዮኮ ቴሌሚዲስን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዲ ድንገታ፣ "እውነት ነው የማኅበረሰባችን አስተሳሰብ በዚህ ረገድ መቀየር አለበት" ይላሉ።
የማኅበረሰቡን ለሕክምና ሂደቶች የሚሰጠውን አረዳድ ሲተቹም፣ "…መርፌ ሳያዝልኝ ነው በኪኒን የላከኝ፤ ዛሬ ደግሞ ራጅ እንኳ ያላዘዘ ሐኪም ነው የገጠመኝ" ብሎ በሐኪሙ ቅር የሚሰኝ ብዙ ሰው መኖሩን አያይዘው ያነሳሉ።
"ይህ አስተሳሰብ እኛንም ፈተና ውስጥ ከቶን ነበር። አሁን ግን ኅብረተሰቡ እየለመደን ነው፤ እኛም የጤና መረጃን በጥራት በማቅረብ እምነቱን ለማግኘት እየሰራን ነው" ይላሉ።
ዮኮ የማማከር የሕክምና አገልግሎት (ቴሌሜዲሲን) የተጀመረው የኮቪድ-19 ወረርሽን ከመከሰቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው።
ይሁን እንጂ በጤና ዘርፍ በተለያየ ስፍራ ይሰሩ የነበሩት መስራቾቹ የኮቪድ-19 ወረርሽኙ ከገባ ወዲህ ምሥረታውን ማፋጠን እንዳለባቸው ተሰማቸው።
ምክንያቱ ደግሞ ወረርሽኙን ተከትሎ ሆስፒታሎች እየተራቆቱ በመምጣታቸው ነው። ሰዎች ሆስፒታል መሄድ ከፈሩ በጤና ለመቆየት ሐኪማቸውን በስልክ ማግኘት አለባቸው። ይህ ሁኔታ ቀደም ብሎ ተጸንሶ የነበረውን ዮኮ ቴሌሜዴስንን አዋለደ።
"በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች የሆስፒታል ደጆችን መርገጥ ፈሩ። ከበድ [ክሮኒክ] በሽታ ያለባቸው ሰዎችም ሆስፒታል አይሄዱም ነበር። በዚህ የተነሳ የቴሌሜዲሲን አስፈላጊነት ከምንጊዜውም በላይ ጎልቶ ታየን" ይላሉ አቶ አብዲ።
ቴሌሜዲሲን በአገራቸው አዲስ ዘርፍ ይመስላል።
ሐሳቡ ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ታማሚውና ሐኪሙ በአካል ሳይገናኙ በስልክ ብቻ በመገናኘት ማቀበል ነው።
አቶ አብዲ ድርጅታቸው የሚሠራቸው ተግባራትን በአራት አምዶች ይቦድኗቸዋል።
የመጀመርያው በሽታን ማወቅና መለየት እንዲሁም ስለ ሕክምናው መወያየት ነው።
ሁለተኛው ተራ የሚመስሉ ግን ጠቃሚ መረጃዎችን ከታማሚው ጋር መወያየት ነው። "እርግጥ ነው በጤና ዘርፍ ተራ የሚባል መረጃ የለም" የሚሉት አቶ አብዲ ትንሽ የጤና ምክር ስህተት ለትልቅ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል ያወሳሉ።
ተራ የሚባል ከታማሚው የሚሰጥ መረጃም በአንጻሩ ለሐኪሙና ለሕክምናው መሳካት ትልቅ ግብአት እንደሚሆን በመግለጸወ፣ የጥቃቅን መረጃን አስፈላጊነት ያስረዳሉ።
"አንድ ሰው ከሐኪሙ ጋር ውሎ መድኃኒት ገዝቶ ቤቱ ገብቶ ስለ መድኃኒቱ አወሳሰድ ግራ ቢገባው ደውሎ ከሐኪሞቻችን ጋር ሊወያይበት ይችላል" ይላሉ።
ወይም ደግሞ አንድን የሕክምና ሂደት [ፐሮሲጀር] ለማድረግ ያሰበ ታማሚ የሕክምና ሂደቱን በተመለከተ ሊያውቃቸው የሚገቡ ቅድመ ጥንቃቄና ድኅረ ጥንቃቄዎችን ከሐኪሞቹ በተጨማሪ በስልክ ከዮኮ ሐኪሞች ሊመከር ይችላል።
ሌላው የቴሌሜዲሰን አገልግሎት አንድ ታማሚ በአካል ሆስፒታል ሄዶ ታክሞ ከሐኪሙ ጋር የነበረው ቆይታ ግን አደናጋሪ ቢሆንበትና ተጨማሪ መረጃን ቢሻ፤ ስልክ ደውሎ ይህንኑ አገልግሎት ማግኘት ይችላል። በጤና ረገድ ተጨማሪ ሐሳብ መስማት የብዙ ተማሚዎች ፍላጎት እንደሆነ ሳይዘነጋ።
ሦስተኛው የቴሌሜዲስን አገልግሎት የድንገተኛ የስልክ ሕክምና አገልግሎት ነው።
አይበለውና አንድ ሰው ቤት ውስጥ ወይም መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና በቅርብ ያለው ሰው የመጀመርያ እርዳታ ለመስጠት ፈልጎ ነገር ግን ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ቢገባው፤ የስልክ ጥሪ በማድረግ በዚሁ ከሰለጠኑ ሐኪሞች ዘንድ አስፈላጊውን እርዳታን ማግኘት ይችላል።
እነዚህ በአራት አምድ የቆሙ ግልጋሎቶች ከጠቅላላ ምክር አገልግሎት ጋር ማቅረብ ነው የቴሌሜዲስን ግብ።
ከአራቱ አገልግሎቶች በተጨማሪ ዮኮ ጥቅል የጤና... | ቴሌሜዲሲን ምንድነው? የርቀት ሕክምና በኢትዮጵያ ይሠራል? | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 409 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በዚህ የተቆጡ ፈረንሳያውያን ወደ ጎዳና ላይ የወጡ ሲሆን የተወሰኑትም ድንጋይና ተቀጣጣይ ነገር በፖሊስ መወርወራቸውን ተከትሎ ግጭት ተፈጥሯል ተብሏል። የጋዜጣ መሸጫ ኪዮስክና መኪኖች የተቃጠሉ ሲሆን በርካቶችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በፓሪስ 46 ሺህ የሚሆኑ ተቃዋሚዎች መውጣታቸውን የአገር ውስጥ ሚኒስትር የገለፀ ሲሆን በርካቶቹ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ቢገልፁም የተወሰኑት ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።
እስካሁን ድረስ 46 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ 20 ፖሊሶችም ተጎድተዋል።
ህጉ የፕሬስ ነፃነትን ይቃረናል፤ የፖሊስ ጭካኔንም ለመዘገብ እክል ይፈጥራል ይላሉ ተቃዋሚዎች።
"ረቂቅ ህጉ የፕሬስ ነፃነት ላይ እክል የሚፈጥር ነው። የማወቅና የማሳወቅ መብትን እንዲሁም ራስን በነፃነት የመግለፅ መብት ጋር የሚጣረስ ነው" በማለት ከተቃውሞ ሰልፈኞቹ መካከል መናገሩን አጃንስ ፍራንስ ፐሬስ ዘግቧል።
መንግሥት በበኩሉ ፖሊሶች በበይነ መረብ ከሚደርስባቸው ትንኮሳና ጥቃት ለመጠበቅ ነው ይላል።
ቅዳሜ እለት ከፓሪስ በተጨማሪ በፈረንሳዮቹ ቦርዶክስ፣ ሊሌ፣ ሞንትፔሊየር፣ ናንቴስና ሌሎች ከተሞችም የተቃውሞ ሰልፎች ነበሩ።
በዚህ ሳምንት ሶስት ነጭ ፖሊሶች አንድ ጥቁር የሙዚቃ ፕሮዲውሰር በዘረኝነት ተነሳስተው ሲደበድቡት የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቶ ነበር.
ሚሸል ዜክለር በፖሊስ ሲደበደብና በቡጡ ሲነረት የሚያሳይ ቪዲዮ በርካቶችን አስደንግጧል።
የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሁኔታውን "አሳፋሪ" ና "ተቀባይነት" የሌለው ያሉ ሲሆን በፖሊስና በዜጎች መካከል ያለው እምነትም እንደገና እንዲገነባ እቅድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል።
በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ፖሊሶችም ከስራ ታግደው ምርመራ እየተከናወነባቸው ነው።
በተለየ ዜና ፖሊስ በመዲናዋ ጊዜያዊ የስደተኞች መጠለያን ማፍረሱን ተከትሎ ከስደተኞችና ተሟጋቾች ጋር ግጭት ተፈጥሯል። በዚህም ላይ ፖሊስ ሙሉ ሪፖርት እንዲያቀርብ ትእዛዝ ተላልፏል።
ረቂቅ ህጉ ለምን አወዛጋቢ ሆነ?
በአገሪቱ ታችኛው ምክር ቤት ድጋፍ የወጣው ረቂቅ ህጉ ምክር ቤቱ እንዲያፀድቀው እየተጠበቀ ነቅ። ከረቂቅ ህጉ ውስጥ አንቀፅ 24 እንደሚያትተው በስራ ላይ ያሉ ፖሊሶች "አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጉዳት" ለማስከተል በሚል ፎቶ ማንሳትም ሆነ ቪዲዮ መቅረፅ በወንጀል ያስቀጣል ይላል።
ህጉን ተላልፈው የተገኙም አንድ አመት እስርና 53 ሺህ 840 ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
መንግሥት እንደሚለው ረቂቅ ህጉ ሚዲያም ሆነ ግለሰቦች የፖሊስን ጥቃት ሪፖርት የማድረግ መብታቸውን አይከለክልም፤ የረቂቅ ህጉ ዋና አላማ ለፖሊስ ጥበቃ ለመስጠት ነው በማለት ይከራከራል።
ተቃዋሚዎች ግን እንደሚሉት ባለፈው ሳምንት እንደተፈፀመው ጥቁር ግለሰብ በፖሊስ ሲደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮ አይጋለጥም ነበር ይላሉ።
ረቂቅ ህጉ ከፍተኛ ትችን ማስተናገዱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂን ካስቴክስ አንቀፅ 24ን ለማሻሻል ኮሚሽን አቋቁማለሁ ብለዋል።
| በፈረንሳይ ፖሊሶችን ቪዲዮ መቅረፅ የሚከለክለው ረቂቅ ህግ ቁጣን ቀሰቀሰ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 327 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቼ ይቆማል?\nትምህርት፣ ስራና ሌሎችም እንቅስቃሴዎች ሲቆሙ የጉዞ እገዳዎችም ተጥለዋል። ስብሰባም ሆነ ሌሎች ማህበራዊ መስተጋብሮች እንዳይደረጉ ታግደዋል።
መንገዶች፣ ካፍቴሪያዎች እንዲሁም የገበያ ስፍራዎች ፀጥ ብለዋል፤ ከተሞች ኦና ሆነዋል በጥቅሉ ዓለም ተዘግታለች ማለት ይቻላል።
• የአሜሪካ እስር ቤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት እስረኛ መልቀቅ ጀመሩ
• የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎችን ገቢ ክፉኛ የጎዳው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ
• የዓለም ጤና ድርጅት ወጣቶች ኮሮና ሊቋቋሙት አይችሉም አለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቆሞ ህይወት ወደነበረበት የሚመለሰው መቼ ነው? ብዙዎች በአእምሯቸው የሚያውጠነጥኑት ነገር ነው።
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እንግሊዝ በሶስት ወራት ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ትገታለች ብለዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻልም ግን የቫይረሱ ማብቂያ ገና እንደሆነ ተናግረዋል።
ወረርሽኙን ማስቆም ረዥም ጊዜ ምናልባትም ዓመታት ሊወስድ ይችላል ሲሉም ፍርሃታቸውን ገልፀዋል።
የማህበረሰቡን እንቅስቃሴዎች መግታትና እገዳዎችን መጣል ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን አይችለም። እገዳዎቹን ዘላቂ ለማድረግ መሞከር ደግሞ ከባድ፣ የረዥም ጊዜ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስን ይፈጥራል።
አገራት የሚያስፈልጋቸው የጣሉትን እገዳ ማንሳት የሚያስችላቸውን ስትራቴጂ መንደፍና የሰዎች ኑሮን ወደ ነበረበት እንዲመለስ ማድረግ እንደሆነ እየተገለፀ ነው።
ምክንያቱም ኮሮናቫይረስ በዚህ ጊዜ ይጠፋል የሚባል አይደለም።
ግን ደግሞ ምን ዓይነት ስትራቴጂ እገዳዎችን ማስነሳት ይችላል? የሚለው አሁንም የአገራት ራስ ምታት ነው።
እገዳውን ማስቀጠልም ማንሳትም የሚያስከትሉት ቀውስ ፈርጀ ብዙ ነው።
በኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ማርክ ውልሃውስ "በምን ዓይነት ስትራቴጂ ከዚህ እንወጣለን? እንዴት? የሚለው ትልቁ ችግራችን ነው" ይላሉ።
አክለውም "እንግሊዝ ብቻም ሳትሆን ማንም አገር ከዚህ ቀውስ መውጫ ስትራቴጂ የለውም" ብለዋል።
ይህ በእጅጉ የገዘፈ ማህበራዊና ሳይንሳዊ ፈተና ነው ይላሉ።
ከኮሮናቫይረስ ቀውስ መውጫ ሶስት መንገዶች
ክትባት፣ በቂ የሚባሉ ሰዎች ቫይረሱን መቋቋም የመቻል ተፈጥሯዊ መከላከያ ማዳበርና በዘላቂነት የግለሰቦችና የማህበረሰብ ባህሪ መቀየር እንደ አማራጭ የተቀመጡ ነገሮች ናቸው።
ዓለም የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ለመድረስ ቢያንስ ከአመት እስከ ዓመት ተኩል የሚሆን ጊዜ ይቀረዋል።
ክትባቱ ቢያንስ 60 በመቶ ለሚሆኑ ሰዎች ተሰጥቶ እነዚህ ሰዎች ቫይረሱን የመከላከል አቅም አዳብረው ለቫይረሱ ተጋልጠው እንኳ የማይታመሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የዚህ ክትባት ሙከራ በአሜሪካ ሰው ላይ ባለፈው ሳምንት ተሞክሯል።
• የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን እያደረጉ ነው?
ከጊዜ ጋር እየተደረገ ባለው ሩጫ ምክንያት ክትባቱ በመጀመሪያ እንስሳት ላይ መሞከር የሚባውን መደበኛ አሰራር ሳይጠብቅ በቀጥታ የሰው ልጅ ላይ እንዲሞከር ተደርጓል።
የኤደንብራው ፕሮፌሰር ውልሃውስ ክትባቱን መጠበቅን አገራት እንደ ስትራቴጂ ሊመለከቱት አይገባም ብለዋል።
ተፈጥሯዊ በሽታውን የመቋቋም አቅምን ማዳበርም ቢያንስ ሁለት ዓመት የሚወስድ ጊዜ ነው እየተባለ ነው።
የእንግሊዝ መንግሥት የአጭር ጊዜ ስትራቴጂ ያለው ነገር ቢኖር ሆስፒታሎች እንዳይጨናነቁ ማድረግ ሲሆን ይህ ደግሞ የኮሮናቫይረስ ሞት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይጨምር ይረዳል ተብሏል።
በሌላ በኩል የእንግሊዙ ቁጥር አንድ ሳይንቲስት ሰር ፓትሪክ ቫላንስ ጊዜው በአሁኑ ወቅት ይህን አሁን ብናደርግ በዚህ ጊዜ ያንን እናሳካለን የሚባልበት ወቅት እንዳልሆነ ገልፀዋል።
የዚህ ዓይነቱ ... | በየአገራቱ ለወትሮ የሰው ግርግር የሚያደምቃቸው ከተሞችና ቦታዎች የኮሮናቫይረስ መምጣትን ተከትሎ ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 399 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
አልሸባብ በላሙ በተደጋጋሚ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን የበርካታ ኬኒያውያን ሕይወት ማለፉም ይታወሳል።
የሰዓት እላፊው ከምሽቱ ሶስት ሰዓት እስከ ንጋት አስር ሰዓት ድረስ ይቆያል ተብሏል።
• በአልሸባብ ጥቃት ሶስት አሜሪካውያን ተገደሉ
• "ወንድ ወይ ሴት መሆን ትልቅ ቦታ ለመድረስ አያግዝም ወይ አያስቀርም"
• ሶማሊያውያን፤ አውስትራሊያን ግመሎቻችን መልሺልን እያሉ ነው
በኬኒያ የሚታተመው ስታር ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ፣ የሰዓት እላፊው የተጣለው የጸጥታ ባልደረቦች የሚያደርጎትን የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ ለማገዝ እንዲሁም የሚኖሩ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል እንዲረዳቸው ነው ተብሏል።
የኬኒያዋ ላሙ የባህር ዳርቻ ለሶማሊያ ድንበር ቅርብ ነች።
በስታር ጋዜጣው ላይ የተጠቀሱት የለላሙ ፖሊስ ኃላፊ፣ ሙቻንጊ ኪኦኢ፣ በሰዓት እላፊው ወቅት መኪኖች እንዲንቀሳቀሱ አይፈቀድላቸውም። በቀንም ፖሊስ መኪኖችን ላይ ፍተሻ ያካሂዳል ማለታቸው ተዘግቧል።
እሁድ እለት በጦር ካምፑ ላይ አልሸባብ ባደረሰው ጥቃት ከሰው ሕይወት በተጨማሪ አውሮፕላኖችና መኪኖችም ተቃጥለዋል።
በጦር ካምፑ አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች ተጨማሪ ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል አካባቢያቸውን ለቅቀው ወደ ሌላ ስፍራ ሄደው ነበር።
ከዚህ ቀደም በዝችው የኬኒያዋ ላሙ ከተማ አልሸባብ አድርሶታል በተባለ የመኪና ላይ ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ ሁለቱ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚታወስ ነው።
ወደ ሞምባሳ በመጓዝ ላይ የነበረውን የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አንድ ግለሰብ ካስቆመ በኋላ በርካታ ጥይቶችን እንዳርከፈከፈበት የአይን እማኞች ገልጸው ነበር።
ኬኒያ ወደ ሶማሊያ ጦሯን ያዘመተችው እ.አ.አ. በ2011 ሲሆን ለዚህም ምክንያቴ ነው ብላ የነበረው ከሶማሊያ ወደ ግዛቷ ድንበር እያቋረጡ የሚፈፀሙ ጥቃቶችና እገታዎች በመበራከታቸው ነበር።
በአሁኑ ሰዓት የኬኒያ ጦር በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ስር ሲሆን በምዕራባውያን የሚደገፈውን የሶማሊያ መንግሥት በመደገፍ የሠላም ማስከበር ሂደቱን ይሰራል።
አልሸባብ በሶማሊያና በኬኒያ
መቀመጫውን በሶማሊያ ያደረገው አልሸባብ በምስራቅ አፍሪካ አሁንም የደህንንት ስጋት እንደሆነ መቀጠሉ እየተገለፀ ነው።
አልሸባብ በሶማሊያና በኬኒያ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን የፈፀመ ሲሆን እኤአ በ2013፣ 67 ሰዎችን የቀጠፈው የዌስት ጌት ሞል ጥቃት የሚታወስ ነው።
በ2014 ደግሞ 148 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የጋሪሳ ጥቃት የተፈፀመውም በአልሸባብ ነበር።
በ2017፣ በሶማሊያ ከ500 በላይ ሰዎችን የገደለው በመኪና ላይ የተጠመደው ቦምብ ፍንዳታም የተቀነባበረው በአልሸባብ መሆኑ ይታወቃል።
በ2019 ደግሞ በኬኒያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዱሲት ዲ2 ሕንፃ ላይ የደረሰውና ከ21 ሰዎችን የሞቱበት ጥቃትንም የፈፀመው አልሸባብ ነበር።
የአልሸባብ አማፂያን በሶማሊያና በኬኒያ ላሙ የሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች ላይ የደረሱ የተለያዩ ጥቃቶችን መፈፀሙን በተደጋጋሚ ጊዜ ተናግሯል።
አሜሪካ የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመግታት ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ፈፅማለች።
| ኬኒያ፡ በላሙ ሶስት አሜሪካውያን ከተገደሉ በኋላ የሰዓት እላፊ ታወጀ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 336 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተነስቶ የነበረው እሣት በቁጥጥር ስር ዋለ\nእሳቱ ትላንት ሳንቃ በር በሚባለው የፓርኩ አካባቢ መከሰቱን የገለጹት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ "አሁን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረነዋል" ሲሉ ለቢቢሲ በስልክ ተናግረዋል።
እሳቱ የተነሳበትን ምክንያት ተጠይቀው አንድ የምርመራ ቡድን ወደ አካባቢው መላኩን እና ውጤቱ እንደታወቀ ይፋ እንደሚያደረግ አስታውቀዋል።
"እሳቱ ሰፊ ጉዳት አድርሷል ተብሎ አይታሰብም" ያሉት ዋና አስተዳዳሪው "የተወሰነ ሄክታር የሳር መሬት ተቃጥሏል። መጀመሪያ እሳቱ ሲነሳ የአካባቢው ሰው ስለተቆጣጠረው ያን ያህል ጉዳት አደረሰ ለማለት አይቻልም። የኅብረተሰቡ ተከታትሎ ባያጠፋው ኖሮ ጉዳቱ ሰፊ ይሆን ነበር" ብለዋል።
በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ባለፈው ዓመት በተደጋጋሚ እሳት መነሳቱ የሚታወስ ሲሆን፤ በሆሌኮፕተር እና ከእስራኤል በመጡ ባለሙያዎች ድጋፍ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
ከዚህ ልምድ በመወስድ በእያንዳንዱ ወረዳ የእሳት አደጋ መከላከል ብርጌድ መቋቋሙን ያስታወቁት አቶ ወርቁ እሳቱ በተለያየ ምክንያት እንደሚነሳ አስታውቀው "ቆላው ላይ በተፈጥሮ እሳት ሊነሳ ይችላል። ይህ ግን [የትላንቱ] ደጋ ስለሆነ በተፈጥሮ ነው የተነሳው ብሎ ለመደምደም አያስችልምም። ለማንኛውም እየተጠና ነው" ብለዋል።
ከተቋቋመው የእሳት አደጋ መከላከል ብርጌድ በተጨማሪ የአካባቢው ማኅበረሰብ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖረው በመደረጉ የዘንድሮው እንደ አምናው ጉዳት አለማድረሱን ገልጸዋል።
በአውሮፓዊያኑ 1978 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ባለፈው ዓመት እሳት ተነስቶ ሰፊ ጉዳት ካደረሰ በኋላ በጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
በዚህም ሳንቃ በር እና መስገጎ በሚባሉ ቦታዎች 330 ሄክታር በላይ ቦታ ተቃጥሎ ነበር።
| ትላንት [አርብ] በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተነስቶ የነበረው እሣት በቁጥጥር ስር ዋለ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 212 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ።
336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ።
እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል።
"ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል።
ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር።
የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር።
ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል።
| ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 183 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ሳዑዲ አረቢያ የጣለችው እገዳ ለየመን ጥፋት ነው\nሳዑዲ አረቢያ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በኢራን እየታገዙ ነው ስትል ትወቅሳለች፤ ቴህራን ከዚህ ተግባሯም እንድትቆጠብም አሳስበዋል።
ኢራን በበኩሏ ለሁቲ ታጣቂዎች ምንም ዓይነት እርዳታ እያደርኩ አይደለም ስትል ክሱን ውድቅ ታደርጋለች።
ዕለተ ቅዳሜ ወደ ሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ የተተኮሰ ሚሳዔል በሳዑዲ ተመቶ እንደወደቀ ይታወሳል።
የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን "ለአማፂያን የጦር መሣሪያ ማቅረብ ከጦርነት አይተናነስም" ሲሉ ተሰምተዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አማባሳደር ኒኪ ሄሊ ሚሳዔሎቹ የኢራን ሳይሆኑ አይቀሩም ብለዋል። ኢራን የመንግሥታቱ ድርጅትን ሕግ እየጣሰች ነው፤ ተጠያቂ ልትሆንና እገዳ ሊጣልባትም ይገባል ሲሉ ተድምጠዋል።
ኢራን ወቀሳውን "የሚሳዔል ጥቃቱ አማፅያኑ በሳዑዲ እየደረሳበቸው ያለውን ወረራ ለመዋጋት ያደረጉት የተናጥል ትግል እንጂ የቴህራን እጅ የለበትም" ስትል አጣጥላዋለች።
በሳዑዲ የሚመራው ጥምር ኃይል የሚሳዔል ጥቃቱን ተከትሎ ወደ የመን የሚያስገቡ በሮችን በጠቅላላ ላልተወሰነ ጊዜ ዘግቷል። ነገር ግን ሰብዓዊ እርዳታ በጥብቅ ፍተሻ አልፎ ሊሰጥ እንደሚችል አስታውቋል።
ነገር ግን ጄኔቫ የሚገኘው የቢቢሲው ኢሞገን ፎክስ እርዳታ ድርጅቶች የድንበሮቹ መዘጋትን ተከትሎ ቁጣቸውን እየገለፁ እንደሆነ ዘግቧል።
የዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማሕበር 900 ሺህ ሰዎችን ያጠቃውን ኮሌራ ለመመከት ወደ የመን ያስጫነው የክሎሪን ክኒን ደንበር መሻገር እንዳልቻለ ተናግሯል።
"እኚህ መግቢያ በሮች እስካልተከፈቱ ድረስ በየመን ያለው ቀውስ ሊፈታ አይችልም። ሃገሪቱ ከአሁን በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ትልቅ ችግር ውስጥ ነች" ሲሉ የቀይ መስቀሉ ጄንስ ላርክ ይናገራሉ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባት ሚሊዮን የመናውያን የረሃብ አደጋ ላይ ናቸው ሲል ማስታወቁ አይዘነጋም።
ሃገሪቱ ከውጭ በሚገባ ምግብ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ ስትሆን አሁን ላይ ግን ነዳጅም ሆነ መድሐኒት ለማስገባት እጅግ አዳጋች ነው።
በየመን ግጭት እስካሁን ደረስ 8 ሺህ 670 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 49 ሺህ 960 ሰዎች በአየር ድብደባ ቆስለዋል፤ እንደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፃ።
| የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማሕበር በየመን ያለውን ሁኔታ ለሚሊዮኖች ሕይወት አደጋ ነው ሲሉ ገልፀውታል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 262 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ጅቡቲ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ\nጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅቡቲ ፓርላማ ፊት ቀርበውም ንግግር አድርገዋል፤ አልፎም በሁለት ቀናት ጉብኝታቸው ወቅት የሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ውህደትን እውን ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
ኢትዯጵያ ለአስርታት በተጠቀመበች የጂቡቲ ወደብ በየዓመቱ 1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ-ንዋይ እንደምታፈስ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሻምቦ ፊታሞ ይናገራሉ።
ይህም 70 በመቶ የጂቡቲ በጀት ያክል እንደሆነ ነው ጨምረው የሚያስረዱት። ኢትዮጵያስ ለወደብ ስምምነቱ በምላሹ ምን ይዛ ትቀርባለች? እንዲሁም የስምምነቱ ዝርዝር ምን ይሆን የሚሉት በበርካቶች ዘንድ የሚመላለሱ ጥያቄዎች ናቸው።
ሀገራቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት ወደብ ለማልማት በሐሳብ ደረጃ መስማማታቸው መነገሩ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት አስፈላጊነት ከፍ እንደሚያደርገው እየተነገረ ይገኛል።
"የሁለቱ ሀገራት ስምምነትን ዝርዝር አፈፃፀም ለማየት በሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች የሚመራ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የወደቡ ድርሻ ምን ያህል ይሆናል የሚለውን በቀጣይ የሚሰራ ነው" ይላሉ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ።
ኢትዮጵያ ለበርካታ አመታት እየተጠቀመችበት ላለው የጂቡቲ ወደብ በየዓመቱ ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ-ንዋይ እንደምታፈስ አምባሳደሩ ይናገራሉ።
እንደ አምባሳደሩ አገላለፅ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በነባር ወደቦችም ይሁን ወደፊት በሚሰሩ ወደቦች ድርሻ እንዲኖራት የሚያደርግ ነው። ይህም ማለት ወደቦቹን በጋራ የማልማት ዕድል ኢትዮጵያ ታገኛለች።
አምባሳደሩ "ኢትዮጵያ ወደቦቹን በጋራ የማልማት እድል ስታገኝ የወደቡን አገልግሎት አሰጣጥ እና ለምጣኔ ሃብት እመርታ ቅልጥፍና ሊሰጥ የሚችል የወደብ አገልግሎት እንዲኖር አብራ የማስተካከል፤ ችግሮች ካሉም አብሮ የማረም ስራ መስራት ያስችላታል" ባይ ናቸው።
"ይህ የወደብ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚኖረውን የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያሳይ እና በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት የፖሊሲዎች የማጣጣም ስራም ይሰራል" ሲሉ ይገልፃሉ አምባሳደሩ።
ይህ የወደብ ስምምነት ለሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ውህደቱ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ሲሉም ሃሳባቸውን ያስረግጣሉ።
"ጅቡቲም ሆነ ኢትዮጵያ የጋራ ኢኮኖሚ ውህደት ቀይሰው ብዙ ፕሮጀክቶችን ያካሄዱ ሃገራት ናቸው ኢትዮጵያ በኢትዮ ጅቡቲ ኮሪደር ላይ የ12 ቢሊየን ዶላር ወጪ በማውጣት ባቡርን ጨምሮ የተለያዩ የማስፋፊያ ግንባታዎች እና አዳዲስ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን አካሂዳለች።"
አሁንም ጅቡቲ በኢትዮጵያ እንደ ቴሌኮም ዘርፍ ያሉ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችላቸው የግብርና ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ስምምነት ላይ መደረሱን አምባሳደሩ ጠቅሰዋል።
ይህም የሆነው ኢትዮጵያ የፖሊሲ ለውጥ አድርጋ ለውጭ ባለሃብቶች የቴሌ ኮም ዘርፉን ከፍታ ሳይሆን አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር እና ትስስሩን ለመፍጠር ታልሞ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ለጅቡቲ መንግሥት የኤሌክትሪክ ሐይል፣ ለእርሻ የሚሆን ሰፊ ሄክታር መሬት፣ ለመጠጥ ውሃ የሚሆን የከርሰምድር ውሃ ያለበት ቦታ መስጠቷ ይታወሳል።
| ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሀገር ውስጥ ጉብኝታቸው በተጨማሪ ወደ ጂቡቲ አምርተው ኢትዮጵያ በወደቡ ላይ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 346 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ትምህርቱን በቻይና ያንግትዜ ዩኒቨርስቲ ይከታተል የነበረው ተማሪ ዉሃን ከተማ ለጉብኝት በሄደበት ወቅት በበሽታው መያዙን ከዩኒቨርስቲው የወጣው መግለጫ ያስረዳል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ወደሚኖርበት ከተማ ጂንግዙ ከተመለሰም በኋላ በበሽታው መያዙ ታውቋል።
•ቻይና አሜሪካን ኮሮናቫይረስን አስመልክቶ ፍራቻ እየነዛች ነው ስትል ወነጀለች
•በኮሮናቫይረስ ከተጠረጠሩ አራት አዲስ ሰዎች አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ ተገለፀ
የቢቢሲ ዘጋቢ ኪልያን ኒጋላ ከካሜሮኗ መዲና ያውንዴ እንደዘገበው ይህ ዜና መሰማቱ በካሜሮናውያን ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።
300 የሚሆኑ ካሜሮናውያን በዉሃን የሚገኙ ሲሆን ወደየትም መንቀሳቀስም ስለማይቻል የውሃ፣ ምግብና ሌሎችም ቁሳቁሶች እጥረትም በማጋጠሙ ችግር ላይ ናቸው ተብሏል።
ዩኒቨርስቲው ለተማሪው ቤተሰቦች እንዲሁም ለኤምባሲው ማሳወቁንና ህክምናም እየተከታተለ ነው ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት የሰውነት ሙቀቱ እየተስካከለ እንደሆነ፣ የምግብ ፍላጎቱም መመለሱን እንዲሁም በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ዩኒቨርስቲው በመግለጫው አትቷል።
•ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ሞተ
•ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን በስምንት ቀናት ሆስፒታል ገነባች
በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች በቻይና የሚገኙ ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ መዛመቱን ተከትሎ በርካታ መንግሥታት ከቻይና በተለይም ከዉሃን እንዲያወጧቸው ቢማፀኑም ምላሽ አላገኙም።
ባለፈው ሳምንት በዉሃን የሚገኙ ካሜሮናውያን ለፕሬዚዳንታቸው ፓውል ቢያ ቤጂንግ የሚገኘው ኤምባሲ ምንም እርዳታ እያደረገላቸው እንዳልሆነ እንዲሁም መሰረታዊ የሸቀጥ ፍጆታዎችም እጥረት አለ በማለት ደብዳቤ ፅፈው ነበር።
| ካሜሮናዊው ተማሪ በኮሮናቫይረስ በመጠቃት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 186 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
የወባ ትንኝ
"ቁጥሩ ጨምሯል። . . . ሁሌም በዚህ ወቅት የወባ በሽተኞች ቁጥር ይጨምራል። አሁን ግን ከበፊቱ እየጨመረ እያየን ነው" ሲሉ ይገልጻሉ።
"ምንም የተለየ ምክንያት የለም። ዘንድሮ ኬሚካልም ሆነ የአጎበር ስርጭት ለህብረተሰቡ ተካሂዷል። የተለየ የሚያደርገው የዝናቡ መጠን ጨምሯል። ከፍተኛ ዝናብ ነበር። ይህ ደግሞ ለወባ መጨመር ምክንያት ነው" ሲሉ ምክንያት የሚሉትን ተናግረዋል።
በአካባቢው በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ቢገልጹም በዚህ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ሰው እንደሌለ ጠቁመዋል።
በወባ የሚያያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ደጋግመው የተናገሩት አቶ ሃብታሙ በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በህክምና ተቋማት ህክምና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው ስለ አጎበር አጠቃቀም ትምህርት መሰጠቱትንና በወባ ላይ የሚሠሩ የህክምና ባለሙያዎች በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ እየሠሩ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በአካባቢያቸው ከነሐሴ ወር ጀምሮ በወባ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን በመተማ ወረዳ ጤና ጥበቃ የወባ ኦፊሰር የሺሃረግ አያናው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ካለፉት አምስት ዓመታት አንጻር በአካባቢው ከፍተኛ የሚባል ለውጥ የለውም ያሉት ወይዘሮ የሺሃረግ ባለፉት ጥቂት ወራት ግን ቁጥሩ ማሻቀቡን ገልጸዋል።
ከሳምንት ሳምንት ቁጥሩ እየጨመረ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ከፍተኛ ቁትር መመዝገቡን ጠቁመዋል።
በአካባቢው ያሉ የቀን ሠራተኞችን ጨምሮ ብዙዎቹ አዲስ በወባ የተጠቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኬሚካል ርጭት በቂ ባይሆንም እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው ዘግይቶም ቢሆን አጎበር ባለፉት ጥቂት ሳምንታት እየተከፋፈለ ይገኛል ሲሉ አስረድተዋል።
በተጨማሪም ችግሩን ለመቅረፍም ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን በማፋሰስ እና በማዳፈን እንዲሁም የተቃጠለ ዘይት በመጠቀም እየተከላከሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በክልሉ የወባ ስርጭት ከሳምንት ሳምንት እየጨመረ ይገኛል ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ ማስተዋል ወርቁ ናቸው።
ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት የወባ ስርጭት መጨመሩ የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸው ሆኖም የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ የክልሉ መልክዓ ምድር አቀማመጥ ለወባ መራቢያ ምቹ መሆን፣ የማህበረሰቡ ቁጥጥር እና መከላከል ሥራ መቀነስ እና የአልጋ አጎበር አጠቃቀም እና ትኩረት ለኮሮናቫይረስ በመደረጉ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ አንዲመዘገብ አድረጓል ብለዋል።
እንደአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ ከሆነ በ2012 በጀት ዓመት በክልሉ በወባ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በ2011 ዓመት ከነበረው 66 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
የ2012 በጀት ዓመትን የመጀመሪያ ሦስት ወራት ከሐምሌ 1/2012 ጀምሮ ካሉት ሦስት ወራት ጋር በማነጻጸር አራት በመቶ ጭማሪ እንዳለው ወይዘሮ ማስተዋል ገልጸዋል።
በክልሉ ነፍሰጡር እናቶች እና ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ይበልጥ በወባ ተጠቂ መሆናቸውን እና ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ መጠቃታቸውን አስተባባሪዋ ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች የክልሉን 88% የወባ ስርጭት ይይዛሉ።
የኬሚካል እና የአጎበር ስርጭት እጥረት መኖሩን ጠቁመው ኬሚካል መረጨት ያለባቸው አካባቢዎች ጭምር እንዳልተረጩ ገልጸዋል።
ክልሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ በ53 ወረዳዎች የኬሚካል ርጭት እንዲካሄድ ጥያቄ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ባለው እጥረት ምክንያት በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት ካለመከናወኑም በላይ በዘጠኝ ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ አለመረጨቱን ጠቁመዋል።
ለወባ ተጋላጭ... | አማራ ክልል፡ ባለፉት ሦስት ወራት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 411 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
"የኢትዮጵያ ባህላዊ መድኃኒትና ሕክምና የምዕተ-ዓመት ጉዞ" ('Acentury of Magico-Religious Healing: The African, Ethiopian case (1900-1980)) በሚለው መፅሀፋቸውም በባህል ህክምና ዘርፍ በፅሁፍ የሰፈሩ ጥንቅሮችን፣ የቁጥርና የፊደላት ማስላት፣ መናፍስት፣ ዕፅዋትን፣ ማዕድናትን እንዲሁም የእንስሳት ተዋፅኦ ፈውስን ማግኘት ኢትዮጵያውያን እንዴት ልቀውበት እንደነበር ዳስሰዋል።
አሁንም ቢሆን ለራስ ህመም ጠንከር አድርጎ ማሰር፣ ለጉንፋን ዝንጅብል በማር፣ ለሆድ ድርቀት ተልባን በጥብጦ መጠጣት ብዙ ኢትዮጵያውያን ለራሳቸው ሆነ ለወዳጆቻቸው ፈውስ ብለው የሚመክሯቸው ናቸው።
በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በከተማም በሽታ ባስ ካለለ ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ የተለመደ አይደለም።
"ባህላዊ መድኃኒት ትልቅ ስፍራ ነበረው አሁንም እየተሰራበት ነው። የዘመናዊ ህክምና አቅርቦት ዝቅተኛ መሆን እንዲሁም መወደድ አማራጩን ወደ ባህል መድኃኒት እንዲያዞር አድርጓል" ይላሉ።
ትውልድና እድገታቸው ደሴ ከተማ የሆነው ዶክተር አሰፋ የባህል መድኃኒት ምርምራቸውን በዚችው ከተማ ነው የጀመሩት። ለዚህ ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን እውቀት ለመቅሰምና ለባህል ህክምና ቅርብ ከሆኑት ከእናታቸው በላይ ሰው አላገኙም።
በታሪክ መምህርነታቸው በደሴ ወይዘሮ ስሒን ትምህርት ቤት ከፍተኛ ዝናን ያተረፉት ዶክተር አሰፋ፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ጥናት እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም በባህል መድኃኒት ላይ ሰርተዋል።
"በመንግሥት ፍቃድና ትዕዛዝ እንደ እድል ሆኖ የታሪክ ትምህርት ደረሰኝ እናም እጣ ፈንታዬ ተወሰነ" ይላሉ። በዩኒቨርስቲው ከነበሩት ትልልቅ ምሁራን መካከል ስለ ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ አውርተው አይጠግቡም።
የኢትዮጵያ የባህል መድኃኒት ጅማሬ
የኢትዮጵያ የባህል መድኃኒት ምርምራቸውን ሲጀምሩ "ታሪክ እንዴት ይፃፋል? እንዴትስ መደምደሚያ ላይ ይደረሳል?" የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ የሚያስችሉ መሰረትም አስይዟቸው ነበር።
የባህል መድኃኒት ውርሳችን ዝም ብሎ በኢትዮጵያዊያን ብቻ የበቀለ ነው? ወይስ ከሌላ ሃገር ተፅእኖ አለበት? እሰከ መቼስ ወደኋላ መውሰድ ይቻላል የሚሉትንም ጥያቄዎችንም ለመመለስ ብዙ ፅሁፎችን ዳስሰዋል።
የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ ከፍተኛ ክፍተት አለበት የሚሉት ዶክተር አሰፋ፤ ያንንም ለመሙላት ፅሁፎቹን ከመዳሰስ በተጨማሪ አዋቂዎቹን በማናገር እንዲሁም ስለእፅዋቶቹ በዝርዝር ማወቅ እንደሚያስፈልግ ዶክተር አሰፋ ይገልፃሉ።
መድኃኒቶቹም ሆነ ዕውቀቱ ይጠበቅበታል የሚባሉት ቤተ-ክርስቲያን እንዲሁም መስጊዶችን ፈትሸዋል።
ኢትዮጵያ በባህል መድኃኒት ረዥም ታሪክ እንዳላት ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያደረጉ የተጓዦችን ማስታወሻ እንዲሁም የሪቻርድ ፓንክረስት ፅሁፎችን ያጣቅሳሉ።
"ከቀላል ስብራት ጀምሮ ውስብስብ ተውሳክና እንደ ካንሰር ወይም በተለምዶ መጠሪያው ነቀርሳ የመሳሰሉ የውስጥ በሽታዎችን ማከም ይሞክሩ የነበሩበት አገር ሰዎች መኖሪያ ለመሆኗ፤ በአረብኛ፣ በግዕዝ፣ የማጣቀሻ ፅሁፎችም አሉ" ይላሉ።
የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ የፖለቲካ ታሪኩ ብቻ ነው የሚሉት ዶክተር አሰፋ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ውትድርና፣ የሥርዓተ-ፆታና ሌሎች የታሪኮችን መንገር እንዳልተለመደ ያስረዳሉ።
"እኛ የምናውቀው የእፅዋት ስብስቡን ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለመድኃኒትነትም ይጠቀሙባቸው የነበሩ የማዕድኖች ስብስብ ነበራቸው" የሚሉት ዶክተር አሰፋ "ከነበረባቸው ተፈጥሯዊ ችግርና ጦርነት ኢትዮጵያዊያን ረዥም እድሜ ኖረዋል፤ ይህም በመድኃኒት ምን ያህል የላቁ እንደነበር ማሳያ ነው" ይላሉ።
ክፍተቱ እንዴት ተፈጠረ?... | "የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 378 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች\nፓሪሴንት-ጀርሜይን ጋር የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ እና ከሲቪያ ጋር ሶስት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻሉት ኡናይ ኤምሪ በአርሰናል አመርቂ ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ዛሬ የክለቡ አስተዳደር እንዳሰናበታቸው ገልጿል።
• የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው
• ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ
ክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኝ ድረስ፤ በረዳት አሰልጣኝ እና በቀድሞ የአርሰናል አማካይ ፍሬዲ ሉንበርግ በግዜያዊነት ይሰለጥናል ተብሏል።
መድፈኞቹ ባለፉት 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን፤ ትናንት ምሽት የዩሮፓ ሊግ የምድብ ጨዋታ በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊትና በሜዳቸው በጀርመኑ ክለብ ኢንትራ ፍራክፈርት 2 ለ 1 ተሸንፈዋል።
ለመሆኑ ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ማን ሊተካቸው ይችላል?
ኑኖ ኤስፒሪቱ ሳንቶስ
1. ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ
ኡናይን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱ አሠልጣኖች መካከል በዋነኛነት ስማቸው እየተነሳ ያለው የወቅቱ የዎልቨርሃምፕተን አሠልጣኝ ኑኖ ኤስፔሪቶ ሳንቶስ ናቸው።
ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ዎልቭስን ይዘው በፕሪሚየር ሊጉ ሰንተረዥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ።
ማክሲሚሎኢያኖ አሌግሪኒ
2. ማሲሚላኖ አሌግሪ
ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኡናይ ኤምሪ ከአርሰናል ከተለያዩ በኋላ በማሲሚላኖ አሌግሪ እና በአርሰናል ክለብ መካከል ግንኙነቶች ተጀምሯል።
በቅርቡ ከጁቬንቱስ የተለያዩት አሌግሪ ከአሮጊቷ ጋር ውጤታማ የሚባል ጊዜን አሳልፈዋል።
አሌግሪ ከጁቬንቱስ ጋር አምስት የሴሪያአ እና አራት ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ከማንሳታቸውም በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ለቻምፒያንስ ሊግ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል።
ካርሎ አንቾሎቲ
3. ካርሎ አንቾሎቲ
ናፖሊን እያሰለጠኑ የሚገኙት ካርሎ አንቾሎቲ ሌላው ኡናይ ኤምረን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱት አሰልጣኞች መካከል ይገኙበታል።
• «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ
ጣሊያናዊው አንቾሎቲ የውድድሩ ዘመን እስኪናቀቅ ድረስ ከናፖሊ ጋር ኮንትራት ቢኖርባቸውም፤ አሰልጣኙ ወደ ኤምሬትስ ሊያቀኑ እንደሚችል በስፋት እየተዘገበ ነው።
ብሬንዳን ሮጀርስ
4. ብሬንዳን ሮጀርስ
ሌስተር ሲቲዎች ዘንድሮ ደንቅ የሚባል የውድድር ዘመን እያሳለፉ ይገኛሉ። በብሬንዳን ሮጀርስ የሚመሩት ቀበሮዎቹ ካለፉት 10 ጨዋታዎች አርሰናልን ጨምሮ በድንቅ ጨዋታ 9 ግጥሚያዎችን በድል ማጠናቀቅ ችለዋል።
ብሬንዳን ሮጀርስ ወደ ኢሚሬትስ እንዲያቀኑ የበርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ምኞት ነው።
ማይክል አርቴታ
5. ማይክል አርቴታ
ኡናይ ኤምሪ አርሰናልን እንዲያሰለጥኑ ከመሾማቸው በፊት፤ ክለቡን ለማሰልጠን ስሙ በስፋት ሲነሳ የነበረው ማይክል አርቴታ ነበር።
የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ባለፉት ሶስት ዓመታት ከከማንችሰተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዎላ ሥር ሆኖ የአሰልጠኝነትን ክህሎት ሲማር ቆይቷል።
ረዳት አሰልጣኙ አርቴታ፤ ማንችሰተር ሲቲ ሁለት የፕሪሚር ሊግ ዋንጫ፣ ሁለት የሊግ ዋንጫዎችን እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎች እንዲያነሳ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ፓትሪክ ቪዬራ
6. ፓትሪክ ቪዬራ
ሌላው የቀድሞ የአርሰናል ባለታሪክ አማካይ ፓትሪክ ቪዬራ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው።
• የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች
ቪዬራ የማይረሳውን የአርሰናል ወርቃማ የ2003/4 የድል የውድድር ዘመን አንበል በመሆን ክለቡን መርቷል።
የፈረንሳዩን ኒስ እግር ኳስ ክለብ እያሰለጠነ የሚገኘው ቪዬራ የሚፈለገውን ውጤት እያስመዘገበ ባይሆንም፤ መድፈኞቹ የቼልሲን አርዓያ የሚከተሉ ከሆነ፤ ቪዬራ የአርሰናል አሰልጣኝ... | አርሰናል ክለቡን ለ18 ወራት ያሰለጠኑት ስፔናዊው ኡናይ ኤምሪን ከስራቸው አሰናብቷል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 399 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ለሥራ ቢሮ መሄድ ብሎ ነገር ከናካቴው ሊቀር ይሆን?\nእንቅስቃሴዎች ውስን ይሆናሉ
መኝታን ቢሮ ማድረግ ይቀጥል ይሆን?
እርግጥ ነው ከቤት ሆኖ መሥራት በድኅረ ኮሮናቫይረስ ዘመን ደንብ የሚሆንባቸው መሥሪያ ቤቶች እንደሚኖሩ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
ይህ ሀቅ ከኩባንያ ኩባንያ ቢለያይም ቅሉ፤ ቀጣሪዎች በዚህ አጋጣሚ ሠራተኞቻቸው ከቤት ሲሰሩ ኩባንያቸው ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ እንደሚሆን በትንሹም ቢሆን ተረድተዋል።
በዚህ ሀሳብ ገፍተውበት ቢሮ ድርሽ እንዳትሉ ቢሉንስ?
ይህ የማይመስል የነበረ ነገር በብዙ ኩባንያዎች ዘንድ እየተጤነ ነው።
"ለምን ቢሮ እንከራያለን?"፣ "ለምን በአንድ ቢሮ ሕንጻ ሺህ ሠራተኞች ይርመሰመሳሉ?" ያሉ የሥራ አስፈጻሚዎችና ቀጣሪዎች ቀስ በቀስ ቢሮዎቻችንን ወደ ሠራተኞቻቸው ሳሎን ሊያመጡት ሽር ጉድ ይዘዋል።
ይህ ነገር የከተማን ሕይወት በጠቅላላ ሌላ መልክ ሊያሲዘው ይችላል። ማኅበራዊ ሕይወትና ትዳርም መልኩን ይቀይር ይሆናል።
በዚህ ጉዳይ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉን ሦስት ባለሞያዎችን መርጠናል።
ጭር ያሉ መሐል
መሀል ከተማዎች ጭር ይሉ ይሆን?
ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር)
ሰዎች ማኅበራዊ እንሰሳ ናቸው። ውጤታማ ለመሆን የግድ ፊት ለፊት ከባለጉዳይ ጋር መገናኘት ያሻቸዋል። ለ20 ዓመታት የተደረገ ጥናት ያንን ነው የሚያስረዳው። አንዳንድ ነገሮች አሉ፤ የግድ ከሰው ጋር ስንገናኝ የምናደርጋቸው። ከእነዚያ መካከል አንዱ ዕለታዊ ሥራ ነው።
ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር)
አዲስ ነገር ልንጀምር ጫፍ ላይ ያለን ይመስለኛል። የሰው፣ የቦታና የጊዜ መስተጋብር ሌላ መልክ በመያዝ እየመጡ ይመስለኛል። ከዚህ ወዲያ አንዳንድ ነገሮች በነበሩበት ይቀጥላሉ ለማለት እቸገራለሁ።
ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ)
አንዳንድ ግዙፍ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እያበረታቱ መሆኑ ግልጽ ነው። ትዊተር ይህን ወስኗል። ፌስቡክም እንዲሁ። የባርክሌይ ባንክ ሥራ አስፈጻሚም "7 ሺህ ሠራተኛ ቢሮ ጠርቶ ማርመስመስ ከዚህ በኋላ ያረጀ ያፈጀ ጉዳይ" እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ቢሮ ሄዶ የመስራቱ ነገር ጨርሶውኑ ይጠፋል ባይባልም የቢሮ መሄድ ልማድ እየከሰመ ሲሄድ አነስተኛ፣ መካከለኛና ዋነኛ የከተማ አካባቢዎች እንደየደረጃው መልካቸው መለወጡ የማይቀር ጉዳይ ነው።
ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር)
አንዳንድ ኩባንያዎች "ለምንድነው ሚሊዮን ዶላር ለቢሮ የምንከሰክሰው" ማለታቸው አይቀርም።፡ ከወዲሁ እንደዚያ ማሰብ የጀመሩ አሉ። ይሄ ማለት በትንሹ ሦስት ነገሮችን ጨርሶውኑ ይቀይራል።
አንዱ የከተሞችን ማዕከላት፣ ሁለተኛው የልጅ አስተዳደግ፣ ሦስተኛው ደግሞ የትዳር ግንኙነት ናቸው። ይህ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።
ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ)
እኔ እንደሚመስለኝ በየሰፈራችን፣ ወደ ቢሮ ርቀን ሳንሄድ ሬስቶራንቶች፣ መዝናኛዎች እና ሌሎች የምንፈልጋቸው ነገሮች ወደኛ እየቀረቡ ይሄዱ ይሆናል። ሰዎች በአቅራቢያቸው መገናኘት መጀመር ይፈልጉ ይሆናል። ሌላው ደግሞ ከቤታችሁ ስሩ ስንባል ቦታ ስንሻ በዚያው በሰፈራችን የተሸለ ስፍራ መፈለጋችን አይቀርም።
ይህ ሀቅ ሰፈሮች እንዲያብቡ ሊያደርጋቸው ይችላል።
ቢሮዎች በስፋት በሚገኙባቸው የከተማ ማዕከላትም ለውጦች መኖራቸው አይቀርም። እነዚያ ሰፋፊ የቢሮ ሕንጻዎች ቆመው አይቀሩም መቼስ። የዲዛይን ለውጥ እየተደረገባቸው ወደ መኖርያ አፓርትመን ይቀየሩ ይሆናል።
ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ የኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር)
ከቤት ሥሩ ከተባልን ሁሉም የቤተሰብ አባል ቤት መዋሉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቤታችን ውስጥ ሰፋፊ ቦታ መሻትን ያስከትላል። ካልሆነም በአቅራቢያችን የተመቻቸ ቦታ እንፈልግ ይሆናል።
ለስብሰባ በሳምንት... | ለብዙዎቻችን ቤታችን ቢሯችን ሆኖ ሰንብቷል፤ በኮሮናቫይረስ ተህዋስ ምክንያት። ይህ ጽሑፍ እየተሰናዳ ያለውም በአንድ ከቤቱ እየሰራ በሚገኝ የቢቢሲ ሠራተኛ ነው። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 415 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
• "በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር የተከሰተው ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ነው" የአማራ ክልል ደኀንነትና ጸጥታ ካውንስል
የቅማንት የማንነት ጥያቄስ በምን መልኩ ተጠይቆ ምን አይነት ምላሽ ተሰጠው? የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከውልደት አሁን እስካለበት ደረጃ ድረስ ጉዞው ምን ይመስላል? ቢቢሲ ጉዳዩን በዝርዝር ተመልክቶታል።
ቅድመ - ቅማንት የማንነትና አስተዳደር ጥያቄ
የቅማንት ህዝብ በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሃገር፤ በአሁኑ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች የሚኖር ህዝብ ነው። በተለይ በጎንደር ከተማ ዙሪያ በሚገኙ ላይ አርማጭሆ፣ ወገራና ጭልጋ ወረዳዎች ማህበረሰቡ በብዛት የሚኖርባቸው አካባቢዎች ናቸው።
• የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ
ከ1983 ዓ.ም በፊት በነበረው የመንግሥት አወቃቀርም የብሔር ማንነትን መሰረት ያደረገ ስላልነበር ብሔረሰቡ የጎንደር ክፍለ ሃገር አካል ሆኖ ከአማራው ህዝብ ጋር በብዛት ተቀላቅሎ ይኖር ነበር። የራሱ የተካለለ ልዩ አካባቢና አስተዳደርም እንዳልነበረውም መረጃዎች ያሳያሉ።
የቅማንት የማንነት ጥያቄ መነሻ?
ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በኢትዮጵያ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የብሔር ፌደራሊዝምን መሰረት ያደረገና ስልጣን በፌደራልና በክልሎች የተከፋፈለ ሥርዓት ተመሰረተ።
የቅማንት የማንነት ጥያቄ ይህ ሥርዓት ከሰፈነ በኋላ በ1984 ዓ.ም መነሳቱን በቅማንት ማንነት ዙሪያ ጥናት ያካሄዱት አቶ ቹቹ አለባቸው ያስረዳሉ።
"የቅማንት ብሔረሰብ ጥያቄ ከየት ወደየት-ከማንነት ጥያቄ እስከ የራስ አስተዳደር ጥያቄና የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ" በሚለው ፅሁፋቸው፤ ጥያቄው በቅማንት ህዝብም ተቀባይነት ያልነበረው ሲሆን ለግለሰቦቹ የተሰጣቸውም ምላሽ "የያዛችሁት ሐሳብ ከአማራ ወንድሞቻችን ጋር የሚያጋጭ ነው፣ ስለሆነም አንቀበላችሁም" የሚል እንደነበረ ጥናቱ ያሳያል።
• በጎንደር የተለያዩ ዞኖች በተከሰተ ግጭት 39ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ
በሕዝቡ ተቀባይነት ካጣ በኋላም ጥያቄው ለአስራ አምስት ዓመታት ያህል ተዳፍኖ ሳይነሳ መቆየቱን ይኸው ጥናት ያመላክታል። የ1999 ዓ.ም የሕዝብና ቤት ቆጠራ ግን አዲስ ክስተት ይዞ መጣ።
የማንነት ጥያቄ ባይነሳም በ1984 ዓ.ም በተካሄደው ሕዝብና ቤት ቆጠራ የቅማንት ሕዝብ በራሱ ተለይቶ 'ቅማንት' በሚል መለያ ኮድ እንደተቆጠረ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዋና የህግ አማካሪ አቶ መርሃ ጽድቅ መኮንን ይናገራሉ።
ነገር ግን ለብቻው ተለይቶ መቆጠሩ አልቀጠለም፤ በቀጣዩ 1999 በተካሄደው ሕዝብና ቤት ቆጠራ ግን ኮዱ ተሰርዞ 'አማራ ወይም ሌላ' በሚል የቅማንት ሕዝብ እንዲቆጠር መደረጉን ያስረዳሉ።
ይህ ሁኔታ ቅሬታን እንደፈጠረና ጥያቄዎችም መቅረብ መጀመራቸውን የሚናገሩት አቶ መርሃ ጽድቅ፣ በተለይም ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ማመልከቻ ይዘው ወደ ክልሉ መንግሥት መምጣት መጀመራቸውን ያስታውሳሉ።
የቅማንት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይርሳው ቸኮልም በአቶ መርሃ ጽድቅ ሃሳብ ይስማማሉ። "ቅማንት ሆነን ሳለ ለምን 'ሌላ' ተባልን በሚል ተሰባስበን ጥያቄውን ጀመርን" ይላሉ።
• የሰሜን ጎንደር ሕዝበ ውሳኔ
የቅማንትን ሕዝብ አምስት በመቶ ድምጽ ማለትም 18500 ድምጽ ሰብስበው ማንነታቸው እንዲታወቅ ለክልሉ መንግሥት ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን አቶ ይርሳው ይጠቅሳሉ።
የቅማንት የማንነት ጥያቄ በተደራጀ መልኩ መቅረብ የጀመረው በዚህ ወቅት ነው።
የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ማንነት ጥያቄ ምላሽ
የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄንም ለመመለስ የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት ጥናት እንዲጠና አድርጓል። የአቶ ቹቹ ጽሁፍ... | የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት? | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 408 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ግን ይህ ታሪኩን የምናጋራችሁ አባት ከአቅሜ በላይ ሆኖ የቁም ቅዠት ሆኖብኛል ይላል። ስቲቭ ይባላል፤ የሚወደው ልጁ ከተራ ጌም ተጫዋችነት አልፎ አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ላይ የደረሰ ሱሰኛ ሆኗል።
ከዚህም ባለፈ መቆጣጠር የማይችለው የቁማር ሱስ ውስጥ ተዘፍቋል።
"ልጄ በጌሞች እንዲህ ይሆናል ወይም መጨረሻው የቁማር ሱስ ይሆናል ብዬ በፍጹም ገምቼ አላውቅም።''
• የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን?
የስቲቭ ልጅ በሃያዎቹ መጀመሪያው ውስጥ የሚገኝ ወጣት ነው። በልጃቸው ምክንያት ስቲቭና ባለቤቱ ለሦስት ዓመታት ተሰቃይተዋል። ''እኛ ያየነውን መከራ ማንም ቤተሰብ ማየት የለበትም። ልጃችን የቁማር ሱሰኛ መሆኑን ስናውቅ ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ገብቶን ነበር።''
የስቲቭ ልጅ ለትምህርቱ የሚሰጠውን ሳምንታዊ ወጪውን በደቂቃዎች ውስጥ የሚያጠፋ ሲሆን ከአቅሙ በላይ ሲሆንበትም ቤተሰቦቹን አማክሯቸው ነበር። እነሱም በዚሁ የሚገላገሉ መስሏቸው ማንኛውም ቤተሰብ እንደሚያደርገው ሙሉ እዳውን ከፈሉለት። ነገር ግን ብዙ ነገሮች ተከትለው መጥተዋል።
ከአንድ ከዓመት በኋላ ስቲቭ ልጃቸው ከእራሱ አልፎ የሰዎችን ገንዘብ እያስያዘ መቆመር መቀጠሉን ሲሰማ በጣም ነበር ያዘነው። የሚያስይዘው ገንዘብ ደግሞ እጅጉን የተጋነነና ትልቅ እዳ ውስጥ የዘፈቀው ነበር።
''በበይነ መረብ ካርታ ነበር የሚጫወተው። እጅግ አስፈሪ ሁኔታ ነበር።''
• እንወራረድ፡- የጦፈው የውርርድ ንግድ በአዲስ አበባ
ስቲቭና ባለቤቱ ልጃቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳለ የተረዱት በዚህ ወቅት ነው። ምን ማድረግ እንዳለባቸውም ሆነ ማንን ማማከር እንዳለባቸው ምንም ዓይነት እውቀቱ አልነበራቸውም።
''የቁማርተኛው ቤተሰቦች መባልን በመፍራትና ልጃችን ገንዘብ የተበደራቸውን ጎረቤቶች ዓይን ላለማየት እራሳችንን ከማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እስከ ማገድ ሁሉ ደርሰን ነበር።''
''ተስፋ ቆርጠን ፊታችንን ወዴት ማዞር እንደምንችል ግራ ገብቶን ነበር። ለራሳችን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ለብዙ ወራት ምርምሮችን ስንሰራም ነበር'' ይላል ስቲቭ።
በሠሩት ጥናት መሠረትም የልጃቸው ሱስ የጀመረው ገና የ12 ወይም የ13 ዓመት ታዳጊ እያለ እንደሆነ ደርሰውበታል። መጀመሪያ አካባቢ የሚያዘወትራቸው ጨዋታዎችም እግር ኳስና የመኪና ውድድር የመሳሰሉትን ነበር።
በወቅቱ መኝታ ቤቱ ውስጥ ሆኖ ለሰዓታት ጌሞቹን የሚጫወት ሲሆን ጓደኞቹም ተመሳሳይ ነገር ያደርጉ ስለነበር፤ ብዙም አሳስቦን አያውቅም ይላል ስቲቭ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ሲያስታውስ።
"ጨዋታዎቹ ምን ዓይነት እንደሆኑና ምን ዓይነት ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙ ምንም የማውቀው ነገር አልበረም" የሚለው ስቲቭ ከመጀመሪያው ጀምሮ ተከታትዬው ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ ላይፈጠር ይችል ነበር ብሎ ያስባል።
''ለረጅም ሰዓታት እግር ኳስ በመጫወት የተጀመረው ሱስ ቀስ በቀስ ወደ ቁማር ሱስ ተቀይሯል።''
በቅርቡ የተሠራ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው 55 ሺህ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ11 እስከ 16 የሚደርሱ የእንግሊዝ ታዳጊዎች አሳሳቢ የሚባል የቁማር ሱሰኞች ሲሆኑ ቤተሰቦቻቸው ስለሱሳቸው ብዙም አያውቁም።
• በዩቲዩብ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው የሰባት ዓመቱ ህፃን
ከሦስት ዓመታት ትግል በኋላ ስቲቭ የአስተማሪነት ሥራውን ትቶ ልጆች የቁማር ሱስ ውስጥ እንዳይገቡ የሚያስተምርና ቤተሰቦችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት አቋቁሟል።
''ነገር ግን በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው። ቤተሰቦች ልጆቻቸው ለረጅም ሰዓታት ኢንተርኔት ላይ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ምን እየሠሩ ነው ብለው ሊጠይቁ ይገባል'' ይላል።
ልጆች ምን ዓይነት ጌሞችን እንደሚጫወቱ መጠየቅ፤ ቢቻል ደግሞ አብሮ ለመጫወት... | የወላጆች ራስ ምታት እየሆነ የመጣው የልጆች የጌም ሱስ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 411 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ለየት ያለው የታይላንድ የማሳጅ ጥበብ በባህላዊ ቅርስነት ተመዘገበ\n'ኑዋድ ታይ' የተባለው ይህ ባህላዊ መታሻ ጥበብ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፉ ባህሎችና የተለያዩ ተግባራት በሚመዘገብበት የሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኗል።
በዚህም ለቀጣይ ትውልድ ተጠብቀው መቆየት ካለባቸው ባህላዊ ተግባራት መካከል አንዱ ተደርጎ እንዲመዘገብ ሆኗል።
• ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . .
• ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?
እነዚህ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ዝርዝር ለተለያዩ ግንባታዎችና ቦታዎች ዕውቅና ከሚሰጠው ከዓለም የቅርሶች ዝርዝር የተለየ ነው።
ባህላዊ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እስካሁን በሦስት ዘርፎች የተከፈሉና ከ127 አገራት የተወጣጡ 550 ቅርሶች ተመዝግበዋል። በዝርዝሩ ውስጥ በየዓመቱ የተለያዩ ቅርሶች ተመዝግበው ይካተታሉ።
ይህ የታይላንድ የማሸት ጥበብ ከሌሎች የተለየ ሲሆን በተለያዩ የሰውነት አቅጣጫዎች በኩል በመሆን የተለያዩ ተከታታይ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ መሆኑም ተነግሯል።
• ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ
• 600 ዓመታትን ያስቆጠረው የሣር ድልድይ
የ'ናኡድ ታይ' ባለሙያዎች የማሸቱን ተግባር ሲያከናውኑ ምንም አይነት ቅባትም ሆነ ዘይት የማይጠቀሙ ሲሆን እጃቸውን ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜም ክንዳቸውንና ጉልበታቸውንም ይጠቀማሉ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የባህልና የሳይንስ ተቋም (ዩኔስኮ) እንዳለው ይህ ተግባር ከጥንት ጀምሮ በታይላንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የነበረ ሲሆን በግብርና ሥራ ላይ የጡንቻ ህመም ሲገጥማቸው በየመንደሩ ያሉ የማሸት ሙያ ያላቸው ሰዎች ጋር በመሄድ ይታሹ ነበር።
በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች መዝገብ ውስጥ ከሚካተቱት መካከል መዝሙርና ዘፈኖችን ጨምሮ የተነገሩ ታሪኮች ሲኖሩበት እነዚህም ለቀጣይ ትውልድ ተጠብቀው ቢተላለፉ ጠቃሚ ይሆናሉ የተባሉትን ነው።
| ጠንከር ያለው የታይላንድ ባህላዊ ጀርባን የማሸት ዘዴ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጠው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ተመዘገበ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 221 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በድንበር አካባቢ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማንሳት ጀመሩ\nየሁለቱም ሃገራት ወታደሮች በሚንቀሳቀሱባት በደቡብ ኮሪያ የምትገኘው ፓንሙጆም መንደር የተጀመረው የማጽዳት ሥራ የተሳካ እንደነበር ተገልጿል።
እዚህ ውሳኔ ላይ ተደረሰው ሁለቱ የኮሪያ መሪዎች ኪም ጆንግ ኡን እና ሙን ጄ ኢን ባለፈው ወር ፒዮንግያንግ ውስጥ ከተስማሙ በኋላ ነው።
• አቶ መላኩና ጄነራል አሳምነው ለማዕከላዊ ኮሚቴ ተመረጡ
ከዚህ በተጨማሪም የታጠቁ ኃይሎች ፊት ለፊት ሆነው ድንበር የሚጠብቁበት የወታደራዊ ቀጠና በሚቀጥሉት 20 ቀናት ውስጥ ነጻ እንደሚሆን የደቡብ ኮሪያው መከላከያ ሚኒስትር ገልጸዋል።
ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ በድንበሮቹ በቅርብ ርቀት የሚገኙት የጥበቃ ቤቶች እንዲሁም ከባድ መሳሪያዎችን በማንሳት ያልታጠቁ ወታደሮችን ብቻ በቦታዎቹ ለማስቀመጥም ታስቧል።
• ህገወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ ቻይናውያን ታሰሩ
ባለፈው ሚያዚያ ደቡብ ኮሪያ በድንበር አካባቢ ትላልቅ የድምጽ ማጉያዎችን በመጠቀም ስታስተላልፋቸው የነበሩትን ፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳዎች እንደምታቆም ገልጻ ነበር።
ወታደራዊ ቀጠናው 250 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 4 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለውና እስከ ኮሪያ ሰርጥ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን፤ እጅግ ከባድ በሚባሉ ተቀጣጣይ ፈንጂዎች፣ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችና የጠበቃ ካሜራዎች የታጠረ ነው።
• በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት
ከዚህ በተጨማሪ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የታጠቁ ወታደሮች በሁለቱም የድንበሩ አካባቢዎች ጥበቃ ያደርጋሉ።
ባለፈው ህዳር ወር አንድ የሰሜን ኮሪያ ወታደር ቀጠናውን በማለፍ ወደ ደቡብ ለማለፍ ሲሞክር በራሱ ሃገር ወታደሮች ተተኩሶበት መቁሰሉ ይታወሳል።
| የሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ ወታደሮች በድንበር አካባቢ ተቀብረው የነበሩ ከ800 ሺህ የሚበልጡ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን ማጽዳት መጀመራቸውን የሃገራቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 204 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በአማካኝ አንድ አርሶ አደር የጡረታ ጊዜውን ክፍያ ድምር 50 ሺህ ፓውንድ ሊያገኝ ይችላለ። ሰፋ ያለ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ደግሞ ይህ ክፍያ በእጥፍ አድጎ በአማካኝ 100 ሺህ ፓውንድ ይከፈላቸዋል።
ይህ የጡረታ ክፍያ በሰፋፊ እርሻዎች ላይ አርሶ አደሮች ከባቢያቸውን እንዲንከባከቡ የሚያበረታታው የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴ አካል ነው። ሆኖም ይህንን ሀሳብ አንቀበልም ያሉ በዕድሜ የገፉ አርሶ አደሮች አሉ።
አሁን ላይ የእንግሊዝ አርሶ አደሮች በቀደመው የአውሮፓ ህበረት ስርዓት ባላቸው የእርሻ መሬት ልክ ድጋፋ የሚደረግላቸው ሲሆን በአማካኝ ወደ 21 ሺህ ፓውንድ ያገኛሉ።
ምንም እንኳን እንደ ንግሰቲቱ ያሉ ሰዎች ባላቸው ግዙፍ የእርሻ መሬት ልክ በዓመት እስከ ግምማሽ ሚሊዮን ፓውንድ ቢከፈላቸውም።
በዌልስ ያሉ አርሶ አደሮችም በአዲሱ የዩኬ መንግስት የጡረታ ክፍያ ውስጥ እንደሚካተቱ ይጠበቃል።
ታዲያ እንደ አካባቢ ጠበቃ ባለሙያው ጆርጅ ኢውስተስ ገለጻ የአውሮፓ ህብረት የአርሶ አደሮች የድጋ ስርዓት አከባቢን ለመታደግና አርሶ አደሮችን ከስጋት ለማላቀቅ ያግዛል።
አዲሱ የዩኬ መንግስት በጡረታ የማግለል ሀሳብ ደገሞ አርሶ አደሮቹን በሌሎች የስራ መስኮች እንዲሰማሩ ያበረታታል በለዋል።
ከ 10 አርሶ አደሮች ወደ 4 የሚጠጉት ዕድሜያቸው ከ 65 በላይ ሲሆን አማካኙ ደግሞ 59 ነው።
| የዩኬ መንግሥት ዕድሜያቸው የገፉ አርሶ አደሮችን ጡረታ እንዲወጡ ሊከፍል ነው | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 177 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በእንግሊዝ የጤና ሚኒስቴር ውስጥ የክትባት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሜሪ ራምሴ ሌሎች አገራት የክትባት ዘመቻቸውን በስኬት እስከሚያጠናቅቁ እና ይህንንም ተከትሎ ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ እነዚህ ገደቦች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ብዙ ሰው የሚታደማቸው ዝግጅቶች ጥንቃቄ የተሞላበት የደህነንት መመሪያዎች ትግበራ እና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸውም ተናግረዋል።
ዶክተር ራምሴ እንዳሉት በተለይም ጭምብሎችን እንደማድረግ ያሉ ገደቦች በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን እያገኙ የመጡ ሲሆን ይህም በተለይ ኢኮኖሚው እንዲንቀሳቀስ እድል ከፍቷል ብለዋል።
‹‹ሰዎች ከእንዲህ ያሉ ገደቦች ጋር እየተለማመዱ አብረዋቸው መኖር ይችላሉ። ኢኮኖሚውም ከባድ ካልሆኑ ክልከላዎችን ጋር መንቀሳቀስ ይችላል›› ብለዋል።
‹‹የኮሮናቫይረስ ቁጥር በሌላው ዓለም እስከሚቀንስ እና ክትባት በበቂ ሁኔታ እስከሚዳረስ ድረስ እነዚህ ገደቦች በእርግጠኝነት ለተወሰኑ ዓመታት የሚቀጥሉ ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ህይወት እንመለሳለን›› ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል።
ዶክተር ራምሴ ጨምረው ቫይረስ በቀላሉ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠቃ ስለሚችል ‹‹በችኮላ ወደ መዘናጋት መግባት የለብንም›› ሲሉም አሳስበዋል።
የእንግሊዝ መንግሥት ዋና የጤና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ በያዝነው ወር መጀመሪየ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ እጅ መታጠብ፣ ጭምብል ማጥለቅ፣ ምርመራ በማድረግ መለየት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ክትባት መጀመር ቫይረሱን ከበጋው ወራት በፊት ለመቆጣጠር ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎ ነበር ብለዋል።
መንግሥትን የሚያማክሩ የሳይንትስቶች ቡድንም የቫይረሱን ስርጭት ሊቀንሱ የሚችሉ መሰረታዊ የሆኑ ፖሊሲዎችን መተግበር ለተወሰነ ግዜ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ነበር።
እነዚሁ ባለሙያዎች በምርመራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መለየት፣ ራስን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ማቆየት፣ በፈቃደኘነት የሚደረጉ እና በሽታውን አደጋዎች ለመቀነስ የሚያበረታቱ ሕዝባዊ መልዕክቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉም ተናግረው ነበር።
የእንግሊዝ መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ቀስ በቀስ ለማንሳት ያዘጋጀው ፍኖተ ካርታ እንደሚለው ማህበራዊ መራራቅን የሚያስገድዱ ሕጋዊ ግዴታዎች ከሰኔ 14 በፊት እንደማይነሱ ያስረዳሉ።
| ኮሮናቫይረስ፡ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና ጭምብል ማድረግ ለዓመታት ሊዘልቅ እንደሚችል ተጠቆመ | amh_Ethi | validation | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 252 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ለ41 ዓመታት በኔዘርላንድ የኖሩት አቶ ሲራክ አስፋው ዘውዱ ቤታቸው የገባው በአጋጣሚ እንደሆነ ይናገራሉ
ለ41 ዓመታት በኔዘርላንድ የኖሩት አቶ ሲራክ አስፋው ዘውዱ ቤታቸው የገባው በአጋጣሚ እንደሆነ ይናገራሉ። የጥገኝነት ጥያቄና ሌላም ጉዳያቸው ተጠናቆ ወደ ሌላ ቦታ እስኪሄዱ ድረስ የግል ሰነዶቻቸውን ጨምሮ ሌሎችም እቃዎች አቶ ሲራክ ቤት በአደራ የሚያስቀምጡ ሰዎች ነበሩ።
ከአራት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያለውን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርስ አቶ ሲራክ ቤት ይመላለሱ ከነበሩ ሰዎች አንዱ ትተውት እንደሄዱም ይናገራሉ።
ሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን
ዘውዱ የማን ነው? መቼ የነበረ ዘውድ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተፈጥረዋል። አንዳንዶች በላሊበላ እንዲሁም በፋሲለደስ ወቅት የነበረ ነው ቢሉም፤ ኒው ዮርክ ታይምስ ያናገረው በኢትዮጵያ ቅርሶች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረገው ጃኮፖ ጊንስቺ፤ ዘውዱ ከሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን በ1990ዎቹ የተሰረቀ ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል።
• ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ
• አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት
በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆነው ጃኮፓ እንደሚለው፤ ዘውዱ ከመጥፋቱ በፊት በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ አንድ የቤተ ክርስቲያን ቄስ ዘውዱን ራሳቸው ላይ ጭነው ፎቶ ተነስተዋል። ዘውዱ በአይነቱ የተለየ እንደሆነ የሚናገረው ተመራማሪው፤ ዋጋውንም 55 ሺህ ዶላር አድርሶታል።
ከመቐለ 16 ኪሎ ሜትር በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኘውና ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረው የሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስትያን ውስጥ በርካታ ንዋየ ቅድሳት እንዳሉ ይነገራል። በተለይም ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስትያኑ እልፍ ንዋየ ቅዱሳን ማበርከታቸውን ቤተ ክርስትያኑ ግቢ ውስጥ ለዓመታት የኖሩ አባቶች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።
ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ82 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ
ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ82 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ፤ ሦስት ዘውዶችን ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስቲያኗ መስጠታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ1745-1865 በወቅቱ የእንደርታ ዙሪያ የሚባለውን ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩት ራስ ወልደሥላሴ በአራት ቦታዎች ማለትም በጨለቆት፣ በአንጣሎ፣ በፈለግዳሮና በመቐለ ቤተ መንግሥቶችን ገንብተው ነበር። በአንድ ወቅትም ጨለቆትን ዋና ከተማቸው አድርገዋታል።
• ከላሊባላ ጥገና ጀርባ ያለው ማን ነው ?
• "የዘረፉትን ቅርስ በውሰት እንመልስ ማለታቸው ተገቢ አይደለም" ሚኒስትር ሂሩት ካሳው
ራስ ወልደሥላሴ ካበረከቷቸው ዘውዶች መካከል አሁን በኔዘርላንድ የተገኘው ዘውድ አንዱ ሲሆን፤ ከ24 ዓመታት በፊት መሰረቁንና ከዚያም መሰወሩን ተናግረዋል።
ዘውዱን በመስረቅ የተጠረጠረው የቤተ ክርስቲያኑ አቃቤ ነዋይ (ጠባቂ)፤ ከአምስት ዓመታት እስር በኋላ ቅርሱ ሳይገኝ መለቀቁን ገልፀው "መንግሥት ኃላፊነቱን አልተወጣም" በማለት የትግራይ አስተዳደር ላይ ቅሬታቸውን ያሰማሉ።
ከሰሞኑ የዘውዱን መገኘት ዜና የሰሙት አባ ገብረሥላሴ፤ ምንም እንኳን ጥልቅ ደስታቸውን ቢገልፁም "እንዴት ተወሰዶ፣ እንዴትስ ነው እየተመለሰ ያለው የሚል ጥያቄ በውል መመለስ ይኖትበታል" ሲሉ አበክረው ይጠይቃሉ።
ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የተወሰደ አንድ ዘውድ ኔዘርላንድ ውስጥ መገኘቱንና በቅርቡ ወደ አገሩ እንደሚመለስ የሰማው የአከባቢው ማኅበረሰብ ዘውዱ የሥላሴ ጨለቆት ስለመሆኑ ቅንጣት ታህል አይጠራጠርም።
ለ41 ዓመታት በኔዘርላንድ የኖሩት አቶ ሲራክ አስፋው
ቄስ ንጉሠኃጎስ ላለፉት ሦስት ዓመታት የቤተ ክርስትያኑ ዓቃቤ ነዋይ በመሆን እያገለገሉ... | የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 408 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉብኝት\n''ለጉብኝት የዛሬ አምስት ዓመት ወደ ግብጽ የመጣው ኢትዮጵያዊ አንድ ወዳጁ እቃ እንዲያደርስለት ይጠይቀዋል። እንደተባለውም እቃውን ወደ ግብጽ ይወስዳል። ይዞት ወደ ግብጽ የመጣው እቃ (ጫት) ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ሰው እንደልቡ የሚጠቀመው ነገር ቢሆንም ግብጽ ውስጥ ግን ክልክል ነው ተብሎ በፍተሻ ወቅት በቁጥጥር ሥር ይውላል።"
የዚህ ኢትዮጵያዊ ታሪክ እጅጉን አሳዝኖኛል ያሉት በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ታዬ አጽቀሥላሴ፤ እስከሚፈታባት ቀን ድረስ ለአምስት ዓመታት በእስር ላይ እንደነበር ገልጸዋል።
''ይህ ሰው ሥራውን አጥቷል፤ ሕይወቱ ተመሰቃቅሏል። በዚህ ሁሉ ዓመት የእስር ቤት ቆይታው፤ ፍርድ ቤት የቀረበው የዛሬ ሦስት ወር ነበር።" በማለት በእስር ቤት ውስጥ ብዙ እንግልት እና ስቃይ እንደደረሰበት አምባሳደሩ ተናግረዋል።
መፈታቱን እስካሁን ድረስ እንዳላመነ እና ከመፈታቱ ባለፈ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በአንድ አውሮፕላን ወደ ሃገሩ መመለስ በመቻሉ ደግሞ እጅግ መደሰቱን ገልጸዋል።
ከእስር ከተፈቱት ሰዎች በተጨማሪ ኤርትራ ውስጥ የነበሩ እና በቅርብ ወደ ግብጽ የገቡት የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት ኮሎኔል አበበ ገረሱ እና የኦህዴድ መሥራችና ሥራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ ዮናታን ዲቢሳ ወደ ሃራቸው ተመልሰዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በግብጽና ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ ጋር የነበራቸው ውይይት ምን እንደሚመስል አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴን ቢቢሲ አነጋግሯቸዋል።
በውይይቱ ወቅት በመሪዎቹ መካከል የነበረው የእርስ በእርስ መግባባት እና መከባበር በጣም አስገርሞኝ ነበር በማለት የጀመሩት አምባሳደር ታዬ፤ ''እስካሁን ባየሁት ነገር የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ብዙ ርቀት እንደሚጓዝ ተሰፋ አደርጋለሁ'' ብለዋል።
ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከልም አንዱ፤ ሁለቱን ሃገራት ያስተሳሰረው የአባይ ወንዝ እና ኢትዮጵያ እየገነባቸው ያለው የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ነው።
ኢትዮጵያ ግድቡን የምትገነባው የግብጽ ሕዝብን ለማስራብ እንደሆነ አብዛኛዎቹ ግብጻውያን ያምናሉ ያሉት አምባሳደሩ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝትም ይህንን አስተሳሰብ ለመቀየር እና የግብጽ ሕዝብን በቅርብ ለማግኘት ነበር ብለዋል።
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የኢትዮጵያ እድገት የግብጽ ልማት ነው በማለት ኢትዮጵያ ለልማቷ በምታደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ የግብጽ ትብብር እንደሚኖር እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለማድረግ ዝግጅትም ፍላጎትም እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
እንደ አምባሳደሩ ከሆነ ሌላኛው መሪዎቹ የተወያዩበት ጉዳይ ሁለቱን ሃገራት ሱዳንንም ጨምሮ በመሠረተ ልማት የማገናኘቱ ሂደት ነበር። ''በውይይቱ መሠረት በባቡር መስመር፤ በአስፋልት መንገድ እና በውሃ ትራንስፖርት ሃገራቱን የማስተሳሰሩ ሥራ እንዴት ማጠናከር እንደሚቻል ተወያይተዋል''።
ከዚህ በፊትም ተቋቁሞ የነበረውን የመሰረተ ልማት ፈንድ የበለጠ ለማጠናከር ደግሞ በመጪው ሃምሌ በካይሮ ስብሰባ ለማድረግ መስማማታቸውን አምባሳደሩ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በትምህርት፤ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስልጠና እንዲሁም በግብርና ሥራ ላይ ለመተባበርም ተስማምተዋል።
እስካሁን የግብጽ ባለሃብቶች 900 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ወጪ ፈሰስ በማድረግ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ተሰማርተዋል ያሉት አምባሳደሩ፤ ተሳትፏቸውን ለመጨመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይም ውይይት ተደርጓል... | ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሁለት ቀናት በግብጽ ያደረጉትን ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ በተለያየ ምክንያት ግብጽ ውስጥ ከነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ገብተዋል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 386 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
የዛላምበሳ ድንበር ከፌደራል መንግሥት ፍቃድ ላልያዙ ተጓዦች ተከለከለ\nበዛላምበሳ መስከረም ወር ላይ የነበረው አዲስ አመት አከባበር
በኢትዮጵያ ድንበር በኩል "ከፌደራል መንግሥት ፈቃድ መያዝ አለባችሁ" የሚል ምላሽ እንተደተሰጣቸውና ከኤርትራ በኩል ደግሞ የይለፍ ወረቀት እየተዘጋጀ መሆኑን" ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
•የትናንትናዋ እለት- በኢትዮ ኤርትራ ግጭት ቤተሰባቸው ለተለያየ?
•መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል?
•የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚመላለሱ መንገደኞች ያለችግር ገብተው መውጣት ይፈቀድላቸው ነበር።
በአሁኑ ወቅት ግን ያለ ይለፍ ወረቀት ከሁለቱም በኩል መንቀሳቀስ አይችልም።
በተጨማሪም በኤርትራ በኩልም ድንበር ጥበቃውን እንዲያጠናክሩ በድንበር ጥበቃ ላይ ለተሰማሩ ከላይ መመሪያ እንደተሰጣቸውም ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ ከኤርትራ መንግሥት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ከራማ ወደ መረብ የሚወስደው የራማ-ክሳድ ዒቃ መተላለፊያ መዘጋቱን የመረብ ለኸ ወረዳ አስተዳደር አቶ ፅጌ ተስፋይ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ማለፍ የሚችሉት ከፌደራል መንግስት የይለፍ ወረቀት ያላቸው ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ተገልጿል።
| ባለፈው የመስከረም ወር የተከፈተው የዛላምበሳ ድንበር ባልታወቀ ምክንያት ከፌደራል መንግሥት ፍቃድ ለሌላቸው ተጓዦች መከልከሉን የጉሎመኸዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረህይወት ገብረየሱስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 169 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
2012፡ የኢህአዴግ መክሰም፣ የተማሪዎች እገታ፣ የምርጫ መራዘም፣ ግድያና እስር\nከእነዚህ ክስተቶች የትኞቹ ጉልህና ወሳኝ ናቸው የሚለውን ለመለየት እንደምንጠቀምበት መመዘኛ የተለያየ ቢሆንም፣ ቢቢሲ በተለይ በለውጥ ሂደት ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው አንድምታ ከፍ ያለ ነው ያላቸውን ጥቂት ክስተቶችን መርጦ ቃኝቷል።
ኢህአዴግ መክሰምና የብልጽግና ውልደት
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አገሪቱን ሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በብቸኝነት የአገሪቱን ሁለንተናዊ ህልውና የመራውና መሠረታዊ ለውጥ በማምጣት ረገድ የአራት የብሔር ድርጅቶች ግንባር የሆነው ኢህአዴግን ያህል የሚጠቀስ ቡድን የለም።
ነገር ግን ከሦስት ዓመት በፊት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሰበት ተቃውሞ ግንባሩ ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ስላላስቻለው የለውጥ እርምጃዎችን ወስዶ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይሞ፤ በ27 ዓመታት ሂደት ውስጥ የቆየበትን ገጽታውን ለመቀየር ሥራውን የጀመረው በዚህ ዓመት ነበር።
ግንባሩ ለዓመታት ሲንከባለል የነበረው አንድ ውህድ ፓርቲ የመሆን እቅዱን በፍጥነት ለማከናወን ወስኖ ከህወሓት ውጪ ያሉት ኦዲፒ፣ አዴፓ እና ደኢህዴን ስምምነት ላይ ደርሰው "ብልጽግና" የተሰኘውን አንድ ወጥ ፓርቲ መሰረቱ። ሂደቱም ከዚህ በፊት የኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎች የሚባሉትን ክልላዊ ፓርቲዎችን አንድ በአንድ በማካተት አገራዊ ቅርጽ ያዘ።
የኢህአዴግ መስራችና በግንባሩ ውስጥ ጉልህ ሚና የነበረው ህወሓት በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ውስጥ ላለመሳተፍ ከወሰነ በኋላ በማዕከላዊው መንግሥት ውስጥ የነበረው ተሳትፎ ቀስ በቀስ እየተዳከመ ከብልጽግና ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፍጥጫ ውስጥ ገባ።
በዚህም ሳቢያ ህወሓት በገዢ ፓርቲነት በሚያስተዳድረው ትግራይ ውስጥ እንቅስቃሴውን በማጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ተቀናቃኝ ሆነ። በቀሪው የአገሪቱ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችንም በማስተባበር "የፌደራሊስት ኃይሎች" የተሰኘ ስብስብን ፈጥሮ በሥልጣን ላይ ካለው ፓርቲ በተቃራኒ ቆመ።
በዚህም በብልጽግናና በህወሓት መካከል በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ያለው አለመግባባት እየሰፋ መጥቶ፣ በግልጽ አስከ መወነጃጀል የደረሰ ሲሆን፤ ይኸው ፍጥጫ ተካሮ ትግራይ ክልል በተናጠል ምርጫ ለማካሄድ እስከመወሰን ደርሷል።
የጃዋር መከበብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የተከፈተባቸው ክስና የተጣለባቸው እገዳ ተነስቶ ወደ አገር ቤት ከገቡ የፖለቲካ ቡድኖች መሪዎችና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ጃዋር መሐመድ በቤቱ አካካቢ ለደኅንነቱ ስጋት ነው ያለውን እንቅስቃሴ ተከትሎ የፈጠረው አለመጋጋት ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኖ ነበር።
ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ገደማ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ አካባቢው የጸጥታ ኃይሎች ያልተለመደ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሶ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ደጋፊዎቹ በቤቱ ዙሪያ ከመሰባሰባቸው ባሻገር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃውሞ ተቀስቅሷል።
አለመረጋጋቱን ተከትሎም በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲጠፋ በንብረትም ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሶ ውጥረቱም ለቀናት ዘልቆ ነበር።
ደስታውን የሚገልጽ የሲዳማ ወጣት
የሲዳማና ክልልነት ጥያቄ በደቡብ
ለዓመታት የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማዕከል ከሆነው የደቡብ ክልል በመውጣት ራሱን የቻለ ክልል ለመመስረት ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የሲዳማ ዞን፣ ቀደም ሲል ካጋጠመ ውዝግብ እንዲሁም ደም ካፋሰሰ ግጭትና ጥቃት በኋላ ኅዳር 10/2012 ዓ.ም በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ መቋጫ አግኝቷል።
ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በመራው በሲዳማ ዞን ውስጥ በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ድምጻቸውን ከሰጡ ከሁለት ሚሊዮን በላይ... | በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያውያንን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ሕይወት በበጎም ሆነ በአሉታዊ ሁኔታ የሚነኩ ነገሮች ተከስተዋል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 414 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በካሊፎርንያ የደረሰ የመሬት መንሸራተት 13 ሰዎችን ገደለ\nበአደጋው የተጎዱ ከ160 በላይ ሰዎች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ከመካከላቸው ሃያዎቹ ከአውሎ ንፋስ ጋር የተያያዘ አደጋ እንደደረሰባቸው ሲታወቅ አራቱ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
300 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ 'ሮሜሮ ካንየን' በተባለ ሸለቆ ውስጥ አሁንም መውጫ አጥተው እንዳሉም እየተዘገበም ይገኛል።
ፖሊስ አካባቢው "የአንደኛው ዓለም ጦርነት የተከናወነበት ሥፍራ ይመስላል" ሲል ተናግሯል።
በከባድ ዝናብ ምክንያት በተነሳ ጎርፍ ምክንያት የተከሰተው ይህ የመሬት መንሸራተት አደጋ ዋናውን የክፍለ ግዛቲቱን መንገድ 48 ኪሎ ሜትር ያህል እንደዘጋው ተዘግቧል።
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የሟቾችና የተጎጂዎች ቁጥር በእጅጉ ሊጨማር እንደሚችል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በአንዳንድ ሥፍራዎች አደጋው ባደረሰው ጉዳት ቤቶች ከሥረ መሠረታቸው ተንቀለው የፈረሱ ሲሆን በጣም ትላልቅ ድንጋዮች እዚህም እዚያም ወደቀው ታይተዋል።
ሞንቴሲቶ የተባለችው አካባቢ የእሣት አደጋ ኃላፊ ካፕቴን ዴቭ ዛንቦኒ እንደተናገሩት ማክሰኞ ዕለት ከቦታው የአራት ሰዎችን አስከሬን ማስወጣት ተችሏል።
አሳሽ ውሻ ሞንቴሲቶ በተባለው አካባቢ ተጎጂዎችን በመፈለግ ላይ ይገኛል
ወርሃ ታህሳስ ላይ በግዛቲቱ የደረሰው የሰደድ እሣት አካባቢውን ስለጎዳው ነው የመሬት መንሸራተቱ የደረሰው ሲሉ ባለሙያዎች ይተንትናሉ።
በሰደድ እሣቱ የተጎዳው መሬት በመሰነጣጠቁ ምክንያት ዝናብ ሲያገኘው ለጎርፍ እና መሰል መሬት መንሸራተት አግልጦታልም ብለዋል።
ቢያንስ 30 ሺህ ሰዎች አካባቢውን ለቀው መውጣት እንዳለባቸውም ተነግሯል።
የካሊፎርንያ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ሲጠየቁ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ምክንያቶቹም የተፈጥሮ አደጋዎች ናቸው።
የአሜሪካ ብሔራዊ የአየር ሁኔታ መሥሪያ ቤት እንዳስታወቀው አሁንም ከባድ ዝናብ እና በረዶ ሊጥል እንደሚችል አስታውቋል።
| በአሜሪካ ካሊፎርንያ ክፍለ ግዛት ደቡባዊ ክፍል የደረሰ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ የ13 ሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። | amh_Ethi | validation | tldr | GEM/xlsum | amharic | 222 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
አሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ምርምሮችን ‘ሰልለዋል’ ያለቻቸውን ቻይናውያን ከሰሰች\nበኮሮናቫይረስ ላይ የሚደረግ ምርምርን ሰልለዋል የተባሉ ሁለት ቻይናውያን ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ክሱ የተመሰረተው አሜሪካ ቻይናን በበይነ መረብ ስለላ አምርራ መተቸቷን ተከትሎ ነው።
ባለፈው ሳምንት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ፤ ሩስያ የኮቪድ-19 ምርምር ለመስረቅ ሞክራለች ብለው ነበር።
አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ ናቸው። የንግድ ሚስጥር በመስረቅና ለበይነ መረብ የገንዘብ ምዝበራ በመመሳጠር ተወንጅለዋል።
አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ ናቸው።
ክሱ ምንድን ነው?
ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ ሁለቱ ቻይናውያን መጋቢት ላይ የማስቹሴትስ የባዮቴክኖሎጂ ተቋምን ሰልለዋል። በተቋሙ ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ጥናት እየተደረገ ይገኛል።
ሜሪላንድ የሚገኝ ድርጅት ኮሮናቫይረስ ላይ ምርምር እያደረገ መሆኑን አስታውቆ በሳምንቱ ቻይናውያኑ የድርጅቱን በይነ መረብ ሰርስረው እንደገቡም ተገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ በግላቸው በበይነ መረብ መረጃ ቢሰርቁም፤ አልፎ አልፎ የቻይና ሰላዮች ድጋፍ ያደርጉላቸዋል ተብሏል። ድጋፍ አድርገዋል ከተባሉት መካከል የቻይና የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊ ይገኙበታል።
ከጎርጎሮሳውያኑ 2009 ወዲህ በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የንግድ ሚስጥር እና አዕምሯዊ ንብረት መስረቃቸውን ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
ቻይና የሚኖሩት እነዚህ ግለሰቦች፤ ስለ ኮሮናቫይረስ ክትባት፣ ህክምና እና ምርመራ መረጃ ለማግኘት የባዮቴክ ተቋማትን የመረጃ መረብ ደህንነት ጥሰዋል።
ከአሜሪካ በተጨማሪ አውስትራሊያ፣ ቤልጄም፣ ጀርመን፣ ጃፓን፣ ሊቱኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ስፔን፣ ስዊድን እና ዩናይትድ ኪንግደም ኢላማ ተድገዋል።
ቻይናውያኑ የዩኬን ሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ተቋም፣ የስፔንን የመከላከያ ተቋም እና አውስትራሊያን የፀሐይ ብርሃን ሀይል ተቋም ሰረስረው መግባታቸው በክሱ ተመልከቷል።
ቻይና ለምን ስለላውን ትደግፋቸዋለች ተባለ?
ዐቃቤ ሕግ እንደሚናገረው፤ ግለሰቦቹ ለግል ጥቅማቸው የሚሠሩበት ጊዜ አለ። ከዚህ በፊት አንድ ድርጅት ሚስጥሩን እንዳያጋልጡበት ገንዘብ እንዲከፍላቸው መጠየቃቸው እንደ ምሳሌ ተጠቅሷል።
ከግል ጥቅም ባሻገር ግን ለቻይና መንግሥትም ያገለግሉ ነበር ተብሏል።
ወታደራዊ መረጃ ሰርቀው ለቻይና መንግሥት መስጠታቸው በክሱ ተገልጿል።
በተጨማሪም የሆንግ ኮንግ የዴሞክራሲ አቀንቃኝ እንዲሁም የቀድሞ የቲያናመን አደባባይ ተቃዋሚን የይለፍ ቃል ለቻይና መንግሥት አሳልፈው ሰጥተዋል ተብሏል።
ተባባሪ ዐቃቤ ሕግ ጆን ደምረስ “ቻይና ለበይነ መረብ ወንጀለኞች ከለላ በመስጠት አሳፋሪ የሆኑትን የሩስያ፣ የኢራን እና የሰሜን ኮርያን ጎራ ተቀላቅላለች። ግለሰቦቹ በድካም ያገኘነውን አዕምሯዊ ንብረት ለቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ያስተላልፋሉ” ብልዋል።
የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንያንግ፤ ቻይና አሜሪካ ላይ የበይነ መረብ ጥቃት ከፍታለች የሚለውን ክስ አጣጥለዋል። ኮቪድ-19ን የተመለከቱ ምርምሮችን ለመስረቅ ተሞክሯል የሚለውን ውንጀላም “የማይመስል” ሲሉ አስተባብለዋል።
በያዝነው ወር መባቻ የአሜሪካ የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ዋሪ፤ ቻይናን “የዓለም ብቸኛዋ ፈርጣማ አገር ለመሆን የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም” ማለታቸው ይታወሳል።
ድርጅቱ አሁን ላይ በየአስር ሰዓቱ ከቻይና ጋር የተያያዙ የደህንት ሥራዎች እንደሚያከናውን ተናግረዋል። በተቋሙ ሥር ካሉት ወደ 5,000 የሚጠጉ የደህንነት ጥበቃ የምላሽ ስለላዎች (ካውንተርኢንተለጀንስ) መካከል ግማሹ ቻይና ላይ ያነጣጠሩ... | ቻይና የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር የሚያካሂዱ ቤተ ሙከራዎች ላይ ስለላ እያደረገች ነው ሲል የአሜሪካ የፍትህ ተቋም ወነጀለ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 393 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ስደተኞቹ ባለፈው ሳምንት አርብ ፍርድ ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው ሦስት መቶ ዶላር እንዲከፍሉ ካልሆነ ግን እንደሚታሰሩ እንደተገለፀላቸው ችሎቱ ላይ የኢትዮጵያዊያኑ አስተርጓሚ የነበረችው ብርቱካን ገረመው ለቢቢሲ ገልፃለች።
• ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች
አስሩም ወንዶች ሲሆኑ ከ18 እስከ 38 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ብረቱካን እንደገለፀችው ስደተኞቹ ከታንዛንያ ጋር ዛምቢያን በምታዋስነውና ከዋና ከተማዋ ሉሳካ 750 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቺንሳሊ በተሰኘችው ትንሽ ከተማ ውስጥ ሲሆን ኢትዮጵያዊያኑ ለቀናት ምግብ ሳያገኙ ልብሳቸው እላያቸው ላይ ተቀዳዶ በከፍተኛ አካላዊ ጉስቁልና ላይ ሆነው ነው የተገኙት። ከተያዙት ስደተኞች መካከልም አንዱ በፅኑ መታመሙ ተነግሯል።
• አሜሪካ የመናዊቷ እናት በሞት አፋፍ ላይ ያለ ልጇን እንዳታይ ከለከለች
"በኮንቴነር ከኬንያ ታንዛንያ ፤ ከታንዛያ ደግሞ ወደ ዛምቢያ ክልል እንደገቡ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት" የምትለው ብርቱካን መንገድ ላይ ፖሊስ ሲያስቆማቸው ሾፌሩ እንዳመለጠና ከዚያም ሾፌሩ መኪናውን ነድቶ ወደ ጫካ በመውሰድ ገንዘብ እንደጠየቃቸው እንደነገሯት ገልፃለች።
ብርቱካን ከጉዳዩ ጋር የሚያገናኛት ምንም ነገር ባይኖርም በአካባቢው ኢትዮጵያዊ ሆና በመገኘቷ በማስተርጎም እንድትረዳቸው በአካባቢው የዛምቢያ የፀጥታ ሃላፊዎች በአለቃዋ በኩል መጠራቷን ተናግራለች።
ኢትዮጵያዊያኑ በአስራ አራት ቀናት ውስጥ የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት ካልከፈሉ በውሳኔው መሰረት እስሩ እንዲፀናባቸው እንደሚደረግ በፍርድ ቤት ተገልፆላቸዋል።
• ብሄራዊ ባንክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር የግሉን ዘርፍ ለማገዝ ስምምነቶችን አደረገ
የተወሰኑት ስደተኞች ደቡብ አፍሪካ ዘመዶች ስላሏቸው እነሱን እንዳነጋገረችና ገንዘብ ከፍሎ ለማስለቀቅ መስማማታቸውን እንዲሁም እራሷ የተቻላትን አድርጋ በቀሩት ጥቂት ቀናት ከእስር እንዲለቀቁ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ትናገራለች።
ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን አካባቢው ላይ በቁጥጥር ስር ውለው ሁለት ባልደረቦቿ በተለያየ ጊዜ ተደውሎ ፍርድ ቤት መሄዳቸውን ብርቱካን አስታውሳለች።
| አስር ኢትዮጵያዊያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ ዛምቢያ ላይ በቁጥጥር ስር ዋሉ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 245 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ታንዛኒያዊው ባሕላዊ ማዕድን አውጪ በአንድ ቀን ሚሊየነር ያደረገውን ማዕድን አገኘ።\nባሕላዊ ማዕድን ቆፋሪው ሳኒኑ ላይዘር ያገኘውን የከበረ ድንጋይ ይዞ
ሁለቱ የከበሩ የማዕድን ድንጋዮች እስካሁን በቁፋሮ ከተገኙ መካከል ግዙፎቹ ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ተገምቷል።
አንዳንድ ምንጮች እንዳሉት እስካሁን የተገኘ ግዙፉ የታንዛናይት ማዕድን የሚመዝነው አራት ኪሎ ግራም የማይሞላ ሲሆን የተገኘውም ከ15 ዓመት በፊት እዚያው ታንዛንያ ውስጥ ነበረ።
በሰሜናዊ ታንዛኒያ ነዋሪ የሆነው ባሕላዊ ማዕድን ቆፋሪ ሳኒኑ ላይዘር በቁፋሮ ያገኛቸው ሁለቱ የከበሩ ድንጋዮች 9.2 እና 5.8 ኪሎ ግራም በመመዘን ነው ክብረወሰኑን በመያዝ ግለሰቡንም ለሚሊየነርነት ያበቁት ተብሏል።
ሳኒኑ እነዚህን የማዕድናት መቼ እንዳገኛቸው የታወቀ ነገር ባይኖርም ነገር ግን ዛሬ ለአገሪቱ መንግሥት የማዕድን ሚኒስቴር በአጠቃላይ በ7.8 ቢሊየን የታንዛንያ ሽልንግ ወይም በ3.43 ሚሊየን ዶላር ሸጧቸዋል።
በሽያጩ ወቅት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ስልክ ደውለው ሳኒኑ ላይዘርን እንኳን ደስ ያለህ ብለውታል።
ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም "ይህ የባሕላዊ ማዕድን አውጪዎች ጥቅም ሲሆን ታንዛኒያም ምንያህል ባለጸጋ መሆኗን የሚያሳይ ነው" ብለዋል።
ማጉፉሊ ወደ ስልጣን በመጡበት ጊዜ አገሪቱ ካላት የማዕድን ሃብት ተጠቃሚ እንደሚያደርጉና ከዘርፉ መንግሥት የሚያገኘው ገቢ ከፍ እንዲል እንደሚጥሩ ቃል ገብተው ነበር።
ከሦስት ዓመት በፊት በዓለም ብቸኛው የታንዛናይት ማዕድን ማውጫ ነው የሚባለውን በሰሜናው የአገሪቱ ክፍል ከኪሊማንጃሮ ተራራ ግርጌ የሚገኘውን አካባቢ በጦር ሠራዊታቸው እንዲጠበቅ አድርገዋል።
ታንዛናይት በምድር ላይ በብዛት ከማይገኙ ውድ ማዕድናት መካከል ሲሆን የፔኒሲልቫንያ ዩኒቨርስቲ በአካባቢው የሚገኝ የማዕድን ጥናት ባለሙያን ጠቅሶ እንዳለው ማዕድኑ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ሊመናመንና ሊያልቅ ይችላል።
| ታንዛኒያዊው ባሕላዊ ማዕድን ቆፋሪ አንድ ላይ 15 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሁለት ግዙፍ ውድ የሆነውን ታንዛናይት ማዕድን በማግኘቱ በአንድ ቀን ሚሊየነር ሆነ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 224 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃቸው በ100 ቀናት\nከእነዚህ ድርጅቶች በተጨማሪም የኢንደስትሪ መንደሮችን፣ የስኳር ፋብሪካዎችን፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች አምራች ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር ተወስኗል።
ይህ ውሳኔ የተወሰነው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱንና የዋጋ ግሽበቱን ለመቋቋም፣ የገቢ ማመንጨት አቅምን ለማጠናከርና የወጪ ንግዱን ለማቀላጠፍ በሚል ነው።
ለዚህ ውሳኔ ሌላኛው ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የብድር መጠን ከፍ በማለቱም እንደሆነ ተነግሯል።
ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት?
‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ?
ዶ/ር አብይ በግላቸው ለውጥ ያመጣሉ?
በአሁኑ ሰዓት መንግስት ያጋጠመው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ዜጎችን እየጎዳ መሆኑ ይነገራል።
አበበ መኮንን በአዋሽ መልካሳ የአንድ አነስተኛ መድሀኒት ቤት ሰራተኛ ነው። ባለፉት አራት ወራት ከፍተኛ የሆነ የመድሃኒት እጥረት እንዳለ ይናገራል።
"በርካታ ሰዎች የወባ መድሀኒት ይጠይቁናል፤ ነገር ግን የለንም። በዚህች ከተማ ለአንዳንድ ሕመሞች የሚፈለግ ክንኒም ሆነ መርፌ ማግኘት ከባድ ነው" ይላል።
ሰዎች ከሐኪም የታዘዘላቸውን መድሃኒት ሳይዙ ባዶ እጃቸውን ነው ወደ ቤታቸው የሚመለሱት የሚለው አቶ አበበ በዚህም የተነሳ ሕሙማን ፈውስ ርቋቸው ለመኖር ተገደዋል ይላል።
"የጅምላ አከፋፋዮቹም በመጋዘናቸው ውስጥ ምንም የላቸውም። እነርሱ እያሉት ያለው ዶላር የለም ነው" በማለት ለቢቢሲ ገልጧል።
"175 ብር እንሸጣቸው የነበሩ መድሃኒቶች 900 ብር ገብተዋል፤ ስለዚህም ሰዎች መግዛት አልቻሉም" ሲል ይጨምራል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚያካሄዳቸው ኢንቨስትመንቶች በሚል ትላልቅ ማሺነሪዎችንና ቁሳቁሶችን ከዓለምአቀፍ ገበያ ይገዛል፤ እንደ ባለሙያዎች አስተያየት ከሆነ ደግሞ ይህ ግዢ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት እያሟጠጠና ከፍ ያለብድር ውስጥ የከተተ ነው።
የተከፋፈለ ኃሳብ
በኪዊን ማሪ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ለንደን የምጣኔ ሐብት ምሁር የሆኑት አቶ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) "መንግስት ገቢ ከማያመነጩ እና የዶላር እጥረቱን ከማይቀርፉ ከእንደዚህ አይነት ትልልቅ ግንባታዎች ራሱን መግታት አለበት" ይላሉ።
መንግስት በቁጥጥሩ ስር ያሉትን ተቋማት ወደ ግል ይዞታ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደ ግል አዞራቸዋለሁ ካለ በኋላ በምሁራኑ መካከል አንድ ወጥ አቋም አይታይም ።
የምጣኔ ሐብት ምሁሩ ደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) እነዚህ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ መዛወራቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎትና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፤ እንዲሁም ይላሉ ምሁሩ የዋጋውን ግሽበት ለመቆጣጠር ይረዳቸዋል።
እንደ ዶ/ር ነመራ ከሆነ ግን በአሁኑ ወቅት እነዚህን ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ ማዘዋወር ሀገሪቱን ወደባሰ የኢኮኖሚ ቀውስ መግፋት ይሆናል።
"የሀገሪቱ ሀብት በከፍተኛ ደረጃ በኪራይ ሰብሳቢዎችና በሙሰኞች እጅ ነው የሚገኝው፤ እነዛ ሰዎች ናቸው እነዚህን ድርጅቶች የሚገዙት፤ ይህ ደግሞ በግለሰቦችና ቡድኖች መካከል ያለውን የሀብት ልዩነት ክፍተት ከፍ ያደርገውና ወደ ቀውስ ያመራል። "
በከፍተኛ ሁኔታ በአስመጪና ላኪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ኪራይ ሰብሳቢዎችን የሚቆጣጠር መስፈርት መዘርጋት እንዳለበትም ይመክራሉ።
በአዋሽ መልካሳ የኢንተርኔት ካፌ ባለቤት የሆነው ተክለማርያም "ኢንተርኔት ቀርፋፋ ነው። በተደጋጋሚም ይቆራረጣል። አንዳንዴ ለሁለት ቀን ያህል ተቋርጦ ይከርማል" ሲል ያማርራል።
የ 512 ሜጋ ባይት አቅም ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት ከቴሌ ቢገዛም ቀርፋፋ እንደሆነ ያስረዳል። አገልግሎቱን ከፍ... | የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ወደ መሪነት መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ለውጦች እየተካሄዱ ነው። የኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኢኮኖሚውን ነፃ ለማድረግ በሚል በመንሥስት ይዞታ ስር የሆኑትን ቴሌ ኮሙኑኬሽንን፣ አየር መንገድን በከፊል ወደግል ለማዘዋወር ወስኗል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 433 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ትግራይ፡ የቢቢሲ ዘጋቢ በኢትዮጵያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር ዋለ\nየቢቢሲ ቃል አቀባይ እስሩን በተመለከተ "ስጋታችንን ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ገልጸን ምላሻቸውን እየተጠባበቅን ነው" ብለዋል።
የግርማይንና የሌሎች መታሰርን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የጋዜጠኞች ደኅንነት ተቆርቋሪው ተቋም የሲፒጄ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ "የጋዜጠኞቹና አብረዋቸው የሚሰሩ ሰዎች እስር ያለጥርጥር እራስን ሳንሱር ማድረግና ፍርሃትን ይፈጥራል" በማለት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የታሰሩትን ሰዎች በመልቀቅ በትግራይ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ያለፍርሃት መዘገብ እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል።
ለቢቢሲ የትግርኛ ቋንቋ አገልግሎት የሚሰራው ግርማይ ገብሩ የተያዘው በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ በሚገኝ ካፍቴሪያ ውስጥ ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር ነው።
የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት አምሰቱ ሰዎች የተያዙት ወታደራዊ የደንብ ልብስ በለበሱ ግለሰቦች ሲሆን፤ በሁለት የወታደር ተሽከርካሪዎች በታጀበ መኪና መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
ግርማይን ጨምሮ አምሰት ሰዎች ለምን ተይዘው እንደተወሰዱ ግልጽ አይደለም። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ሪፖርተሩ መቀለ ውስጥ ወደሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ተወስዷል።
ህወሓትን ለማስወገድ በተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ የፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች የትግራይ ክልልን መቆጣጠራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ካስታወቁ በኋላ ካለፈው ኅዳር ጀምሮ ክልሉ በወታደራዊ ዕዝ ስር ይገኛል።
ወታደራዊ ግጭቱ የተባባሰው የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የሠሜን ዕዝ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ ነበር።
በውጊያው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለመፈናቀል ተዳርገዋል፤ በተጨማሪም በክልሉ ተፈጽመዋል የተባሉ ግድያዎችና የሰብአዊ ቀውስ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ ነው።
ወደ ክልሉ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ለወራት እንዳይገቡ ከተከለከለ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ አገር ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ገብተው እንዲዘግቡ ባለፈው ሳምንት ፈቅዷል።
የቢቢሲው ዘጋቢ የታሰረው ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) እና ለፋይናንሻል ታይምስ የሚሰሩ ሁለት ሌሎች ጋዜጠኞቹን የሚያግዙ ባለሙያዎች (ፊክሰር) መታሰራቸው ከተነገረ ከቀናት በኋላ ነው።
ሌላ ታምራት የማነ የተባለ የአገር ውስጥ ጋዜጠኛም ባልታወቀ ምክንያት በወታደሮች ተይዟል።
ባለፈው ሳምንት አንድ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ባለስልጣን "አሳሳች በሆኑ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ላይ መንግሥት እርምጃ ይወስዳል" ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።
ኤኤፍፒ እና ፋይናንሻል ታይምስ ወደ ትግራይ በመሄድ ዘገባ እንዲሰሩ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና በሠላም ሚኒስቴር ፈቃድ አግኝተው ነበር።
"በፍጹም ብርሃኔ ላይ የቀረበ ይህ ነው የሚባል ክስ አልተነገረንም። ከመገናኛ ብዙሃን ጋር መተባበሩ ለመታሰሩ ምክንያት ሊሆን አይገባም፤ ስለዚህም በአስቸኳይ እንዲለቀቅ እንጠይቃለን" ሲሉ የኤኤፍፒ ግሎባል ኒውስ ዳይሬክተር ፊል ቼትዊንድ ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል።
ፋይናንሻል ታይምስ ባወጣው አጭር መግለጫ የታሰሩትን ጋዜጠኞቹን የሚያግዙ ባለሙያዎች (ፊክሰር) ለማስለቀቅ "የሚቻለውን ሁሉ እርምጃ" እየወሰደ መሆኑን ገልጿል።
ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ የመንግሥት ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ድል መቀዳጀታቸውን ቢያውጁም በክልሉ ውስጥ ግጭቶች የቀጠሉ ሲሆን የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አልተናሳም።
| ግጭት በተካሄደበት የሰሜናዊ ኢትዮጵያዋ የትግራይ ክልል የቢቢሲ ዘጋቢ የሆነው ግርማይ ገብሩ በኢትዮጵያ ወታደሮች መታሰሩን ተከትሎ ቢቢሲ ስጋቱን ገለጸ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 373 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በፈረንሳይ ኩሽና ውስጥ ተሰቅሎ የተገኘ ስዕል በ24 ሚሊዮን ዩሮ ተሸጠ\nስዕሉ ለበርካታ ዓመታት በኩሽና ውስጥ ከማብሰያ ምድጃ በላይ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል።
ይህ የስዕል ሥራ ከአንድ ወር በፊት ነበር በሰሜናዊ ፈረንሳይ የተገኘው።
6 ሚሊዮን ዋጋ ያወጣል ተብሎ ቢገመጥም፤ ከተገመተው አራት እጥፍ በሆነ ዋጋ በጨረታ ተሽጧል።
• ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ
• የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው
አጫራጩ ድርጅት በሥም የልተጠቀሰው የስዕሉ ገዢ ከሰሜናዊ ፈረንሳይ እንደሆነ ጠቁሟል።
ስዕሉ ለበርካታ ዓመታት በኩሽና ውስጥ ከማብሰያ ምድጃ በላይ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል። አንድ የስዕል ባለሙያ እና አጫራች ስዕሉን ከተመለከተ በኋላ ባለቤቶቹ የስዕሉን ዋጋ ለማስተመን ባለሙያዎችን እንዲያማክሩ ሲወተውት ነበር ተብሏል።
ባለቤቶቹ ግን ስዕሉ እድሜ ጠገብ ሃይማኖታዊ ምልዕክት ያለው ስዕል ከመሆን ባለፈ ብዙ ዋጋ ያለው የጥበብ ሥራ መስሎ አልታያቸውም።
በስዕሉ ላይ የተደረጉ ጥልቅ ምርምሮች ስዕሉ የጣሊያናዊው ሰዓሊ ሶኒ ዲ ፔፖ መሆኑን አረጋገጥዋል።
በጣሊያን ፍሎረንስ የተወለደው ሶኒ ዲ ፔፖ በ13ኛው ክፈለ ዘመን መጨረሻ ላይ እና በ14ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የስዕል ሥራዎችን ሰርቷል።
ይህ የጥበብ ሥራ በመጠን አነስተኛ ሲሆን 20 ሲ.ሜትር በ26 ሴንቲ ሜትር ያክላል። ስዕሉ የአንድ የስዕል ሥራ አካል ሲሆን የተቀሩት ስዕሎች ሎንደን እና ኒው ዮርክ በሚገኙ የሰዕል ማሳያ ማዕከል ውስጥ ይገኛሉ።
| በዕውቅ ጣሊያናዊ ሰዓሊ ተስሎ የነበረው እና ለረዥም ዓመታት ጠፍቶ የቆየው ስዕል በአንዲት አዛውንት ፈረንሳያዊ ሴት ኩሽና ውስጥ ከተገኘ በኋላ ሪኮርድ በሆነ በ24 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ በጨረታ ተሸጠ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 210 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ቻይና አሜሪካንን በልጣ ከዓለም 1ኛ ሆነች\nትናንት እሑድ ይፋ በተደረገ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት መሠረት ቻይና አዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተው በአጭር የጊዜ ሂደት አሜሪካንን ለመብለጥ ችላለች።
ይህ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው መረጃ እንደሚያትተው ወደ ቻይና ድርጅቶች አዳዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ4 ከመቶ ተመንድጓል።
በሌላ አነጋገር በፈረንጆቹ 2020 ወደ ቻይና የተመሙ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ወደ አሜሪካ ከተመሙት አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች በእጅጉ ያላቁ ናቸው።
ይህ የሚያሳየው ቻይና በዓለም ዙርያ ያላት ተጽእኖ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነው ብሏል ሪፖርቱ።
ከውጭ አገራት ወደ አሜሪካ የሚገቡ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ባለፈው ዓመት (2020) በግማሽ መቀነሳቸውን ዘገባው አትቷል።
ሆኖም ወደ ቻይና የሚተሙ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው የመጡት። በዚህም ምክንያት ነው ቻይና ከአሜሪካ ልቃ እንድትገኝ ያስቻላት።
ቻይና ባለፈው ዓመት ብቻ 163 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገሯ አዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈሶላታል።
አሜሪካ ግን 134 ቢሊዮን ብቻ ነው ወደ አገሯ የቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ የቻለችው።
ይህን አሐዛዊ ዘገባ ያወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በንግድና በልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) ላይ ነው።
በ እአአ 2019 አሜሪካ የ251 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላ ነበር። በዚህ ጊዜ ቻይና የ140 ቢሊዮን የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ነበር ማግኘት የቻለችው።
ምንም እንኳ ቻይና በተገባደደው የፈረንጆች ዓመት አዲስ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ አሜሪካንን ቀድማ አንደኛ ብትሆንም በጠቅላላ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት ግን አሁንም ዓለምን የምትመራው አሜሪካ ናት።
ይህም የሚያሳየው ለዓመታት አሜሪካ የአዳዲስ የውጭ ኢንቨስትመንቶች መዳረሻ ተመራጭ አገር እንደነበረችና የውጭ ኢንቨስትምነት ምን ያህል የተከማቸባት አገር መሆኗን ነው ይላል ሪፖርቱ።
የምጣኔ ሀብት አዋቂዎች ግን በአዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የታየው የአሰላለፍ ልዩነት አሁን ቻይና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ወሳኝ የሆነ ተጽእኖ ማሳረፍ መጀመሯን አመላካች ነው ይላሉ።
በአሜሪካ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2016 የትራምፕን መምጣት ተከትሎ ነበር ወደ 472 ቢሊዮን ዶላር የተመነደገው።
ያን ጊዜ ቻይና 134 ቢሊዮን ዶላር ላይ ነበረች።
ያን ጊዜ የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ኩባንያዎች ቶሎ ቻይናን እየለቀቁ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ከፍተኛ ማበረታቻ እየሰጠ ነበር።
በተመሳሳይ የትራምፕ አስተዳደር የቻይና ኩባንያዎች ለደኅንነት ስጋት ስለሚሆኑ በየጊዜው ይመረመራሉ በሚል በአሜሪካ የነበራቸው ሚና ለማንኳሰስ ሞክሯል።
ይህ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ መንገድ ተጽእኖ ለመፍጠር በመቻሉ ሊሆን ይችላል ባለፉት ዓመታት የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የበላይነት በአሜሪካ ተይዞ የቆየው።
ሆኖም ባለፈው ዓመት (2020) የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮቪድ ወረርሸኝ የተነሳ ሲቀዛቀዝ የቻይና ኢኮኖሚ ግን ቶሎ ማንሰራራት ችሏል።
በ2020 የቻይና የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት መጠን (GDP) በ2.3% ማደጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ።.
ይህም ቻይናን በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የኢኮኖሚ ድቀት ብዙም ያልተሰማት ብቸኛዋ የዓለም አገር አድርጓታል።
ብዙ ኢኮኖሚስቶች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የቻይና ኢኮኖሚ በፍጥነት ማንሰራራቱ አስገርሟቸዋል።
በ2020 በዓለም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በጠቅላላው በ42% ወድቋል።
ብዙውን ጊዜ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የሚባለው አንድ የውጭ ኩባንያ በሌላ አገር ውስጥ ያሉ ኩባንያዎችን በመግዛት ወይም ከራሱ ኩባንያ... | ቻይና በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI) ለመጀመርያ ጊዜ አሜሪካንን በመብለጥ የምድራችን ቁጥር አንድ አገር ለመሆን በቃች። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 413 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
የአገሪቷ ባለሥልጣናት እንዳሉት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ቀድሞ ከነበረው በበለጠ በስፋት እየተዛመተ ሲሆን፤ የበለጠ ገዳይ ነው ተብሎ ግን አይታመንም።
ለንደንን ጨምሮ የደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ ሰፊው ክፍል የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት አዲስ እና ጥብቅ ገደብ ውስጥ ናቸው።
ኔዘርላንድስ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ መከሰትን ተከትሎ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚደረጉ በረራዎችን ማገዷን አስታውቃለች።
እገዳው ከእሁድ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እስከ አውሮፓውያኑ ጥር አንድ ድረስ እንደሚቆይ የደች መንግሥት ገልጿል።
እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በዩናይትድ ኪንግደም ከተገኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ናሙና በመገኘቱ እንደሆነ ተነግሯል።
በዩኬ የተከሰተውን ሁኔታ የበለጠ ግልፅ እንዲሆን እየተጠባበቁ መሆኑን የገለፀው የአገሪቷ መንግሥት፤ "አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ወደ ኔዘርላንድስ ሊገባ የሚችልበትን ሁኔታ በተቻለ መጠን መገደብ አለበት" ብሏል።
የደች መንግሥት አክሎም በቀጣዮቹ ቀናት በዩኬ የተገኘውን የአዲሱን ቫይረስ አደጋ ባለበት ለመቆጣጠር ስለሚያስችለው ሁኔታ ከሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ጋር አብሮ እንደሚሰራ አስታውቋል።
ስለአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የምናውቀው
የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩኬ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
ድርጅቱ እንዳለው ዩኬ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ በተመለከተ እየተካሄዱ ስላሉ ጥናቶች መረጃዎችን ስታጋራ እንደነበር ጠቅሶ፤ ድርጅቱ ስለአዲሱ ቫይረስ ባሕርይ እና አደጋው የደረሰበትን ለአባል አገራቱ እና ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
ምንም እንኳን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው እስከ 70 በመቶ ያህል የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከፍተኛ ሞት ስለማስከተሉ አሊያም በበለጸጉት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ሊበገር ስለመቻሉ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል።
95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር።
| ኮቪድ-19፡ የዓለም ጤና ድርጅት በዩኬ የተከሰተውን አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው አለ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 272 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በክረምት ሲዘንብ የመሬት ሽታ ለምን ያስደስተናል?\nለወራት ዝናብ አጥቶ የደረቀ መሬት በዝናብ ሲርስ ደስ የሚለንና ሽታው የሚያውደን ያለምክንያት አይደለም። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ባክቴሪያ፣ እፅዋትና ብርሀን ተደማምረው ዝናብ ሲጥል ደስ የሚል ሽታ እንዲፈጠር ያደርጋሉ።
• ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም?
ዝናብ ሲጥል ያለው አስደሳች መአዛ 'ፐትሪኮር' ይባላል። ሽታው ዘለግ ላለ ጊዜ ይቆያል። ይህም የተመራማሪዎችና የሽቶ አምራቾችንም ቀልብ ገዝቷል።
'ፐትሪኮር' የሚለውን ስም ያወጡት ሁለት አውስትራሊያውያን ተመራማሪዎች ናቸው። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ ገደማ።
ባክቴሪያ
ዝናብ ደረቅ መሬት ሲነካ የሚፈጠረው ሽታ ምክንያቱ ባክቴሪያ ነው።
ፕሮፌሰር ማርክ በተር እንደሚሉት፤ ዝናብ ሲዘንብ ብዙዎች በተለምዶ "መሬቱ ሸተተኝ" የሚሉት ባክቴሪያ ሞለኪውል ሲሠራ ያለውን ጠረን ነው።
• የዓለማችን 'ጭንቀታም' እና 'ደስተኛ' ሃገራት ደረጃ ይፋ ሆነ
ይህ ሞለኪውል (ጂኦዝሚን) ጤናማ አፈር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ ጸረ ባክቴሪያ (አንቲባዮቲክ) ለመሥራትም ያገለግላል።
ጠብታ ውሀ መሬት ሲነካ ጂኦዝሚን አየር ውስጥ ይለቀቃል። ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ የሽታው መጠን ይንራል። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ሰዎች በቀላሉ ሽታው ያውዳቸዋል።
በ1960ዎቹ ሕንድ ውስጥ እጣን ለመሸጥ ይህ ሽታ ጥቅም ላይ ይውል ነበር። አሁንም ሽቶ አምራቾች ከጂኦዝሚን ሽቶ ይሠራሉ።
ሽቶ አምራቿ ማሪና ባርሴኒላ "ዝናብ ደረቅ መሬትን ሲነካ ያለው ሽታ ድንቅ ሽቶ ይወጣዋል፤ ከብዙ ንጥረ ነገር ጋር ቢዋሀድ እንኳን ሰዎች ሽታውን ይለዩታል" ትላለች።
• ፍየሎችም «ከፍትፍቱ ፊቱ» ይሉ ይሆን?
'ፐትሪኮር' በግሪክ ቋንቋ በአማልክት የደም ሥር የሚዘዋወር ፈሳሽ የሚል ትርጓሜ አለው።
እፅዋት
ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ የእፅዋት መአዛ ከጂኦዝሚን የሚመነጭ ሊሆን ይችላል። ዝናብ ሲዘንብም ሽታው ጎልቶ ይወጣል።
ፕሮፌሰር ፊሊፕ ስቴቨንሰን የተባሉ ተመራማሪ እንደሚሉት፤ እፅዋት ጥሩ ሽታ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ንጥረ ነገር የሚመነጨው በእፅዋት ቅጠል ውስጥ ነው። ዝናብ ይህንን ንጥረ ነገር የሚያጠፋበት እድል እንዳለ ሁሉ፤ የደረቁ እፅዋትን አርሶ ኬሚካል እንዲያመነጩ ያደርጋል።
ዝናብ ሲጠፋ የእፅዋት ሜታቦሊዝም ይጓተታል። ሲዘንብ ሂደቱ ይታደስና እፅዋቱ አስደሳች ሽታ ይፈጥራሉ።
ብርሀን
በዝናብ ወቅት የሚከሰት መብረቅ፤ ልዩ ሽታ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል። ከመብረቁ የሚወጣው ብርሀን የሚፈጥረው ንጥረ ነገር አየር ውስጥ ሲሰራጭ የሰው ልጆችን የሚያስደስት ሽታ ይፈጥራል።
ፕሮፌሰር ማርቢት ስቶልዝበርግ፤ መብረቅ፣ ከመብረቅ የሚፈጠረው ብርሀንና ዝናቡ በጋራ የአየሩን ሽታ ይለውጡታል። አቧራ ተወግዶም በንጹህ አየር ይተካል።
እንግዲህ ተመራማሪዎች ዝናብ ሲዘንብ የሚፈጠረው ሽታ የሚያስደስታችሁ በባክቴሪያ፣ በእፅዋትና በብርሀን ምክንያት ነው ብለዋል። ይህን መረጃ ካገኙ በኋላ ክረምትን በተለየ ሁኔታ ያጣጥሙት ይሆን. . .
| ክረምትም አይደል? አገሪቱ በዝናብ ርሳለች። ለመሆኑ ዝናብ ሲጥል ያለው ሽታ ለምን ደስ እንደሚልዎ ያውቃሉ? | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 332 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከአለም ቅርስ አንዱ የሆነው የማቹ ፒቹ የፍርስራሽ ስፍራ ተዘግቶ የነበረ ሲሆን ጃፓናዊው ቱሪስትም ሰባት ወራት መጠበቅ ነበረበት።
ጄስ ታካያማ ስፍራውን ለመጎብኘት አቅዶ የነበረው መጋቢት ወር ላይ የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጉብኝት በመከልከሉም ሳይሳካለት ቀርቷል።
በቱሪዝም ዘርፉ በርካታ ጎብኝዎች ያሉት ጥንታዊው የኢንካ ከተማ ፍርስራሽ በሚቀጥለው ወርም ላይ በጥቂት ሰዎች ለመክፈት ታቅዷል።
ስፍራው የሚከፈትበት ትክክለኛ ቀን ግን አልተገለፀም።
ጄስ ታካያማ መጋቢት ወር ላይ ወደ ፔሩ ሲመጣ ይህንን ቅርስ ለመጎብኘት የነበረ ቢሆንም በወረርሽኙ ምክንያት መውጣት መግባት ባለመቻሉም በአቅራቢያው ባለች አጉዋስ በተባለች ከተማም ለወራት ያህል ያለ ምንም መሄጃ ጠብቋል።
በዚህም ምክንያት የባህል ሚኒስትሩ አሌሃንድሮ ኔይራ ብቻውን እንዲጎበኝ መፍቀዳቸውን ተናግረዋል።
"ፔሩ የመጣው ስፍራውን የመጎብኘት ህልም ስለነበረው ነው" በማለትም ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ጄስ ታካያማ ለሰባት ወር ጠብቆ ስፍራውን ሳይጎበኝ እንዳይመለስ በሚልም ቅዳሜ እለት የፍርስራሽ ስፍራውን እንዲጎበኝ ተደርጓል።
በማቹ ፒቹ ተራራማ ስፍራም ላይ ሆኖ ለወራት የጠበቀውን ቦታ በመጎብኘቱ የተሰማውን ደስታም መግለፁንም በቀረፀው ቪዲዮ አስተላልፏል።
"ጉብኝቱ በጣም አስገራሚ ነበር፤ አመሰግናለሁ" በማለትም ጄስ መልእክቱን አስተላልፏል።
በአንደስ ተራራዎች የሚገኘው የማቹ ፒቹ ስፍራ የኢንካ ግዛት ማሳያ ሲሆን በጎሮጎሳውያኑ 1450 እንደተገነባም ይታመናል።
በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገበው ይህ ስፍራ አለም ካላት ሰባቱ አስደናቂ ቅርሶችም ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።
ወረርሽኙ ከተከሰተባት እለት ጀምሮ በፔሩ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 849 ሺህ ሲሆን 33 ሺህ መሞታቸውንም ከጆንስ ሆፕኪንስ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
| ፔሩ ሰባት ወር ለጠበቀው ጃፓናዊ ታሪካዊ ስፍራዋን ብቻውን እንዲጎበኝ ፈቀደች | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 219 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ\n'ካምብሪጅ አናሊቲካ' የተባለ የፖለቲካ አማካሪ ተቋም የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋሉን ተከትሎ ነው የማህበራዊ ትስስር ዘዴው ወቀሳው እውነት መሆኑን ያመነው።
ዙከርበርግ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጥ "የግለሰቦች ግላዊ መረጃ ያለአግባብ ተበርብሯል" ብሏል።
ዘግየት ብሎም ከሲኤንኤን ጋር ቃለ-ምልልስ ያካሄደው ዙከርበርግ በሁኔታው 'በጣም ማዘኑን' እንዲሁም ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት የፈፀመ ሰዎች ላይ ደግሞ 'እርምጃ' ለመውሰድ ማቀዱን ተናግሯል።
የአሜሪካ ኮንግረስ ፊት ቀርቦ ስለሁኔታው ማስረዳት መቻሉ እረፍት እንደሰጠው የተናገረው የፌስቡክ አለቃ ዙከርበርግ የሰዎችን ግላዊ መረጃ የሚበርብሩ መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽን) ይህን ማድረግ እንዳያቻላቸው ለማድረግ የማያደርገው ጥረት እንደሌለም አሳውቋል።
"የእርስዎን ግላዊ መረጃ የመጠበቅ ግዴታ አለበን። ይህንን ማድረግ ከተሳነን ግን እርስዎን ለማገልገል ብቁ አይደለንም ማለት ነው" ሲልም በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።
የሰሜን አሜሪካው የቢቢሲ ቴክኖሎጂ ነክ ዘገባዎች ተንታኝ የሆነው ዴቭ ሊ ግን የፌስቡክ ይቅርታ አልተዋጠለትም። "ትልቁ ነገር ጥያቄ ይቅርታ መጠየቁ ሳይሆን ይህ ጉዳይ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ምርመራ መካሄዱ ነው" ሲል ይከራከራል።
ፌስቡክ በአውሮፓውያኑ 2014 ላይ የገጠመውን ዓይነት የመረጃ መሹለክ ክስተት ድጋሚ ማጋጠሙ ትልቅ ትንታኔ የሚፈልግ መሆኑንም ዴቭ ያስረዳል። የሰዎች ግላዊ መረጃ ያለፍላጎታቸው ሲበረበር ማስጠንቀቂያ እንኳን አልደረሳቸውም ይህም ምላሽ ይፈልጋል ባይ ነው ተንታኙ።
ፌስቡክ ላይ ጫናዎች የበረቱ ሲሆን 'ካምብሪጅ አናሊቲካ' የተሰኘው መቀመጫውን ለንደን ያደረገ ተቋም እንዴት አድርጎ የ50 ሚሊዮን ያህል ተጠቃሚዎችን መረጃ እንደበረበረ አሁንም በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።
የአሜሪካው ፌዴራላዊ የንግድ ኮሚሽን ፌስቡክ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ማዘዙን አንዳንድ ዘገባዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ። የአውሮፓ ሕብረትም መሰል እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የአንግሊዝ መረጃ ኮሚሽን ደግሞ ካምብሪጅ አናሊቲካ የተሰኘው ተቋም ላይ ግልፅ ምርመራ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ ነው።
የፖለቲካ አማካሪ ተቋሙ በ2017ቱ የኬንያ ድጋሚ ምርጫም ውስጥ እጁ እንዳለበት ዘገባዎች ከጠቆሙ በኋላ ግልፅ ምርመራ እንዲካሄድ ጫናዎች እየበረቱ ይገኛል።
| የፌስቡኩ ፈብራኪና አለቃ የሆነው ማርክ ዙከርበርግ 'በስህተት' የሰዎች ግላዊ መረጃ ያለፍላጎታቸው መበርበሩንና ለአንድ የፖለቲካ አማካሪ ድርጅት ጥቅም መዋሉን አመነ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 268 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች\nኩባንያ
በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል።
ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል።
• በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ
• ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች
• ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ?
የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር።
በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል።
ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል።
በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል።
ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው።
የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል።
በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል።
በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል።
ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር።
ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል።
ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው።
ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል።
ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
| የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 384 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በክልሉ የማንነት ጥያቄዎችን ላነሱ ወገኖች ምላሽ መስጠቱን ያስታወሰው ይህ መግለጫ ቅሬታ ያላቸው አካላት ጥያቄያቸውን አቅርበው መስተናገድ "የሚችሉበት ዕድል እያለ" በኃይል ፍላጎታቸውን ለማስፈፀም መሞከራቸውን "ጸረ ህገ መንግስትና የለየለት ጸረ ሰላም ተግባር" ሲል ኮንኖታል።
መግለጫው አክሎም "የቅማንት የራስ አሥተዳደር ኮሚቴ የተከተለው አቅጣጫም ፍላጎትን በኃይል በብሔረሰቡና በክልሉ መንግስት ላይ የመጫን "ኢ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ" መሆኑን በመግለጫው ላይ አትቷል።
• "መንገደኞች የሚጓዙት በመከላከያ ታጅበው ነው" የማዕከላዊ ጎንደር ኮሙኒኬሽን
• "የሰለጠነና በሙሉ አቅም የሚዋጋ ኃይል ነው ችግሩን የሚፈጥረው" የማዕከላዊ ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ
ካውንስሉ በመግለጫው ላይ እንደጠቀሰው "ኢ ሕገመንግሰታዊ እርምጃ ለመቀልበስ በተወሰደው እርምጃ" ግጭት መከሰቱንና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አንስቶ ክልሉና የፌደራል መንግሥት "በትዕግስትና በአርቆ አስተዋይነት" ችግሩን ለመፍታት ቢጥሩም ውጤት ሊመጣ አለመቻሉን ገልጿል።
በአካባቢው የተከሰተው ግጭት "አካባቢውን ወደ ተሟላ ትርምስ የሚያስገባና ለክልሉ ብሎም ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት" መሆኑንም የካውንስሉ መግለጫ አመልክቷል።
መግለጫው አክሎም የአካባቢው ሠላም መደፍረስ የገቢና የወጪ ንግድ ላይም ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ጠቅሷል።
በዚህም የተነሳ የፌዴራል የፀጥታ ኃይል መከላከያን ጨምሮ ማንኛውም ህጋዊ እርምጃ ወስዶ ቀጠናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሸጋግር መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል።
የተላለፈውን መመሪያ በመከተል የክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ካውንስል በማዕከላዊ፣ በምዕራብ ጎንደር፣ በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር እና በጎንደር ከተማ ክልከላዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ መመሪያ መሰጠቱን አስፍሯል።
ከመመሪያዎቹ መካከል ማንኛውም የኃይል እንቅስቃሴን የኃይል እርምጃ በመውሰድ መቆጣጠር የሚል የሚገኝበት ሲሆን ጥፋተኞችን ለመቆጣጠር ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃን በመውሰድ የኃይል ተግባርን ፍፁም እንዳይቀጥል ማድረግ የሚል ይገኝበታል።
ካውንስሉ የሠላም አማራጮችን ለማስፋት በሚል በአካባቢው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ግጭት የገቡ ቡድኖችና ግለሰቦች በአስቸኳይ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በመመለስ ያሏቸውን ልዩነቶች እንዲፈቱ ጥሪም አስተላልፏል።
• እውን ድህነትን እየቀነስን ነው?
• ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም"
በግልፅ በታወቁ የፀጥታ ኃይሎች ከተያዙት ትጥቅና መሳሪያ ውጪ በተጠቀሱት የክልሉ ዞኖች ላልተወሰነ ጊዜ ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሲንቀሳቀስ ይዞ የተገኘ ግለሰብ የሚወረስበት መሆኑ ተገልጿል።
የቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ከዚህ ቀደም በተወሰነው ህጋዊ ውሳኔ መሠረት በአፋጣኝ በሕዝብ ይሁንታ የሚደራጅ የራስ አስተዳድርን በማቋቋም ሁሉም አገልግሎት እንዲጀምር እንደሚያደርግም በመመሪያው ላይ ተካትቷል።
በአካባቢው ውስጥ በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ገብተው የነበሩ ኃይሎች፣ ግለሰቦችና ቡድኖች እስከ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለሱ የክልሉ መንግሥት በድጋሜ ይቅርታ ማድረጉም ተገልጿል።
ነገር ግን በሰው ግድያ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ አግባብ የሚታይ መሆኑ በመመሪያው ላይ ተካትቷል።
በየአካባቢው ለሚፈጠሩ "ወንጀሎች ፀረ-ሰላም ድርጊቶችና እንቅስቃሴዎች" ሁሉም አካላት የመቆጣጠር፣ የማሳወቅ፣ እርምጃ እንዲወስድ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ያለው መመሪያው፤ ይህ ካልሆነ ግን ተጠያቂነትን ከማስከተልም በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኘው ትጥቅ ሙሉ በሙሉ ተራግፎ... | "በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር የጥምር ኃይል ሊሰማራ ነው" የአማራ ክልል ደኀንነትና ጸጥታ ካውንስል | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 390 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ቱርክ ታሪካዊውን ሙዚየም መስጂድ እንዲሆን ወሰነች\nቀደም ሲል የቱርክ ፍርድ ቤት ኢስታንቡል ውስጥ የሚገኘው ታሪካዊውና ታዋቂው የባሕል ማዕከል አያ ሶፊያ መስጂድ እንዲሆን የሚያስችል ብይን ሰጥቷል።
አያ ሶፊያ 1500 ዓመታት ታሪክ ያለውና ሲመሰረት ካቴድራል የነበረ ሙዚየም ነው። ከዚያም ኦቶማኖች ካቴድራሉን ወደ ሙዚየምነት ቀይረውት ነበር። ሥፍራው በሙዚየምነት የተመዘገበው በአውሮፓውያኑ 1934 ነው።
የተባበሩት መንግሥታት የቅርስ ጥበቃ ወኪል ዩኔስኮ ቱርክ ድርጅቱን ሳታማክር ሥፍራውን ወደ መስጅድነት እንዳትቀይረው አሳስቦ ነበር።
እርምጃውን በተመለከተም የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ለውጥ ያስፈልጋል ሲሉ ይሞግታሉ።
ቱርክ ውስጥ ያሉ እስላማዊ ድርጅቶች ሥፍራው መስጅድ እንዲሆን ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር። መንግሥትና ሐይማኖት ይነጣጠሉ የሚሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ ይህንን እንቅስቃሴ ሲያወግዙ ከርመዋል።
ሙዚየሙን መስጅድ ሊያደርግ ይችላል የተባለውን ውሳኔ በርካታ ዓለም አቀፍ የሐይማኖት ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ተቃውመውታል።
የምሥራቁ ዓለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኃላፊ ውሳኔውን ተቃውመውታል። ከበርካታ ሚሊዮን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የሚኖሩባት ግሪክም የቱርክን ሃሳብ ተቃውማለች።
የዘመናዊ ቱርክ መስራች ናቸው የሚባሉት ሙስጠፋ ከማል አታቱርክ ናቸው በ1934 ሥፍራው ሙዚየም እንዲሆን የፈቀዱት። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቦታው ከእምነት ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። የትኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው በነፃነት የሚጎበኘው ነበር።
የቱርክ ከፍተኛ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የሆነው 'ካውንስል ኦፍ ስቴት' ግን ዛሬ አርብ ባስተላለፈው ውሳኔ "ሥፍራው መስጅድ ሊሆን ይገባል፤ ይህን ሥፍራ ከዚህ ውጭ ለሌላ ዓይነት ጥቅም ማዋል ሕገ-ወጥ ነው" ሲል በይኗል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቱርክ ፍርድ ቤት አያ ሶፍያን በተለመከተ ላቀረበችው መፍትሄ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ እንሳዘናት አስታውቃለች።
ቤተክርስቲያኒቷ የቱርክ ፍርድ ቤት የወሰነው ውሳኔ ወደ ከፋ ክፍፍል የሚወስድ ነው ትላለች።
| የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶዋን ታሪካዊው አያ ሶፊያ ሙዚየም ወደ መስጂድነት እንዲለወጥ የሚያስችል ውሳኔን በፊርማቸው አጸደቁ። | amh_Ethi | validation | tldr | GEM/xlsum | amharic | 236 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
በአሜሪካ ሲካሄድ የነበረ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ተቋረጠ\nኩባንያው እንዳለው በክትባት ሙከራው ላይ እየተሳተፈ የነበረው በጎ ፍቃደኛ የጤና እክል የገጠመው ክትባት ለማግኘት ከሚደረገው ምርምር ጋር ተያይዞ ስለመሆኑ ይጣራል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፍቃደኞች በሚሳተፉበት ምርምር ላይ በጎ ፍቃደኞች የጤና እክል ሊገጥማቸው እንደሚችል ኩባንያው አስታውሶ፤ ለጥንቃቄ ሲባል ሶስተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የሙከራ ምርምሩ እንቋዲረጥ ተደርጓል ብሏል።
የበጎ ፍቃደኛውን ግላዊ መብት ለመጠበቅ ሲባል የተሳታፊው ማንነት እና ያጋጠመው ህመም እንደማይገለጽ ተጠቁሟል።
የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እንዲቋረጥ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
በዩናይትድ ኪንግደም በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ ጥምረት ሲካሄድ የነበረው ምርምር ላይ አንድ በጎ ፍቃደኛ ላይ የጤና መቃወስ ማጋጠሙን ተከትሎ ሙከራው ከተቋረጠ በኋላ ምርምሩ እንደገና መጀመሩ ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ከ180 በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባት ምርምሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ አንዳቸውም የክሊኒካል ሙከራቸውን ማጠናቀቅ አልቻሉም።
ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ኩባንያ እያካሄደ ያለው የኮሮናቫይረስ ምርምር ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የቻለ ነበር።
ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ሲያካሂድ በነበረው የምርምር ስራ ላይ በጎ ፍቃደኞችን መመልመል የጀመረው መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነበር።
ሙከራው 60ሺህ ተሳታፊዎችን በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ያሳትፋል ተብሎ ነበር።
| ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ሲያካሂድ የነበረውን ምርምር አንድ በጎ ፍቃደኛ መታመሙን ተከትሎ ማቋረጡን አስታወቀ። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 185 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ቀጥለውም "አሁን አገራችንን በኢኮኖሚ የመጠገን ሥራን እናፋፍማለን" ብለዋል።
ጣሊያን 234 ሺህ ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘውባት 33 ሺህ 600 ሰዎች ሞተውባት ነው አሁን መጠነኛ ፋታን ያገኘችው። በወረርሽኙ መነሻ ሰሞን ከዓለም አገራት ቫይረሱ ክፉኛ ካጎሳቆላቸው አገሮች በአንደኛ ደረጃ የምትጠራ አገር ነበረች።
አሁን ባለው ደረጃ ጣሊያን በቫይረሱ የሟቾች ቁጥር አሜሪካንና ዩናይትድ ኪንግደምን ተከትላ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ በተስፋ የተሞላው ንግግራቸውን ያሰሙት አገሪቱ እቀባዎችን በማቃለሉ ሂደት የመጨረሻውን ምዕራፍ በገባደደችበት ወቅት ነው። አሁን የአገር ውስጥ በረረራዎችና ጉዞዎች ተፈቅደዋል፤ ዓለም አቀፍ ድንበሮቿንም እየከፈተች ነው።
"ይህ ወረርሽኝ በአገራችን ሥር ነቀል መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እንድንነሳ እድል ሰጥቶናል፤ አገራችንን በድጋሚ ነድፈን ልንገነባት ይገባል" ብለዋል ጁሴፔ።
ለሕዝባቸው ባደረጉት በዚህ ንግግር ጄሴፔ የግብር እፎይታ ማዕቀፍን ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
ጁሴፔ በዚህ ተስፋን በሰነቀው ንግግራቸው ማብቂያ ሕዝባቸው በፍጹም እንዳይዘናጋ መክረዋል። በተለይም ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅና ጭምብል ማጥለቅ መዘንጋት የለበትም ብለዋል። እነዚህን ቸል ማለት ዋጋ ያስከፍላል ሲሉ አስምረውበታል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ሁሉ የጣሊያኑ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር "ቫይረሱ ሄዷል ብላችሁ አትዘናጉ፤ ቫይረሱ አሁንም አለ" ብለዋል።
ጣሊያናዊያን አሁን ምን ማድረግ ተፈቅዶላቸዋል?
ከባለፈው መጋቢት ወዲህ በጣሊያን የአገር ውስጥ በረራዎች እንዲቆሙ ተደርገው ነበር። ጣሊያናዊን ከቤታቸው ወጥተው መንቀሳቀስም አይቸሉም ነበር፤ እጅግ ለመሠረታዊ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር።
ቱሪዝምም ባለበት እንዲቆም ተደርጎ ነበር። ወደ ጣሊያን እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ዜጎችም ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ሲገደዱ ነበር።
አሁን ግን ከትናንት ረቡዕ ጀምሮ ወደፈለጉበት ክልል መንቀሳቀስ ይችላሉ። ወደ ክፍለ አገር ብቻም ሳይሆን ወደተፈቀዱ የአውሮፓ ከተሞችም መንቀሳቀስ ተፈቅዷል። ነገር ግን ከአውሮፓ አገሮች ውጪ ወደየትም መሄድ አይችሉም።
ሱቆች፣ ካፊቴሪያዎችና ምግብ ቤቶችም በራቸውን ወለል አድርገው ከፍተዋል። እንደ ኮሎሲየም የመሳሰሉ እውቅ የቱሪስት መዳረሻዎችም ተከፍተዋል።
በሌሎች የአውሮፓ አገሮችስ ምን ተፈቅዷል?
ምንም እንኳ ጣሊያን በሯን ለሌሎች የአውሮፓ አገሮች ብትከፍትም ሁሉም ግን በምላሹ ይህንኑ አላደረጉም። ለምሳሌ ኦስትሪያ ለሁሉም የአውሮፓ አገራት ድንበሯን ከዛሬ ጀምሮ የምትከፍት ሲሆን ለጣሊያን ግን "እምብየው፤ ይቆየኝ" ብላለች።
ስዊትዘርላንድ በበኩሏ ድንበሯን ለጀርመን፣ ለኦስትሪያና ለፈረንሳይ ከሰኔ 15 ወዲህ ለመክፈት ያቀደች ቢሆንም ይህንን እድል ግን ለጣሊያን ነፍጋታለች።
ባለፈው ሳምንት ደግሞ ዴንማርክና ኖርዌይ የእርስ በርስ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል። በዚህ ስምምነት ስዊድንን አግልለዋታል። ስዊድን በወረርሽኙ ዙርያ የተለየ ፍልስፍናን በመከተሏ የጉዳት መጠኗ ከፍ ማለቱ እየተዘገበ ይገኛል።
ሦስቱ የባልቲክ አገራት ማለትም ሉቴኒያ፣ ላቲቪያ እና ኢስቶኒያ እርስ በርሳቸው ብቻ አንዱ ለሌላው ድንበሩን ከፍቷል።
ዩናይትድ ኪንግደምና ስፔንን የመሰሉ አገራት ደግሞ ከውጭ ለሚገቡ የለይቶ ማቆያ ሥርዓትን አበጅተዋል።
| የጉዞ እቀባ የተነሳላቸው ጣሊያናዊያን በደስታ እየተቃቀፉ ነው | amh_Ethi | validation | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 360 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣኑን ባቡር በይፋ አስመረቀች\nበምረቃ ሥነ ስርዓቱም ላይ የሞሮኮው ንጉስ መሃመድ ስድስተኛና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባቡሩን ለመመረቅ ከታንጊያር ከተማ ወደ መዲናዋ ራባት ጉዞ አድርገዋል።
• ስሜታዊ ድራማ በሙምባይ ባቡር ጣቢያዎች ውስጥ
• የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ
• ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’
ባቡሩ በሰዓት 320 ኪሎሜትር ወይም 198 ማይል ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህም ከዚህ ቀደም ከካዛብላንካ ወደ ታንጊር ለመሄድ በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር ወይም 124 ማይል ይወስድ የነበረውን በግማሽ ቀንሶታል።
የሞሮኮው አዲሱ ባቡር በደቡብ አፍሪካ መዲና ጆሐንስበርግ ከሚገኘው ኦሊቨር ታምቦ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማዋ የንግድ መናሀሪያ ሳንተን የሚያጓጉዘውን ፈጣን ባቡር በእጥፍ ይበልጠዋል።
ባቡሩ 2.4 ቢሊየን ዶላር (22.9 ቢሊዮን ድርሃም) እንደፈጀና በ7 ዓመታት እንደጠናቀቀ የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።
| ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን የሆነውን ባቡር አስመረቀች ፤ ባቡሩ የንግድ ከተማ ከሆነችው ካዛብላንካ ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከሏ ታንጌር ለመሄድ የሚወስደውን ጊዜ በግማሽ ይቀንሳል። | amh_Ethi | train | tldr | GEM/xlsum | amharic | 144 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
ይህ የወባ መድኃኒት ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ፈውስ እንደማይሰጥ የዓለም ጤና ድርጅትም ሆነ የእርሳቸው የጤና አማካሪዎች በተደጋጋሚ የመሰከሩ ቢሆንም ትራምፕ ግን ወይ ፍንክች በማለት በአቋማቸው ጸንተዋል።
እንዲያውም "ሃይድሮክሲክሎሮኩዊን እያጣጣላችሁት ያላችሁት እኔ ጥሩ ነው ስላልኩ ነው" ብለዋል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ።
ትዊተር የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ይዘት ያለው አሳሳች ተንቀሳቃሽ ምስልን አጋርቷል በሚል ሰሌዳውን አጥፍቶበት ነበር።
ዶናልድ ትራምፕ ይህን አወዛጋቢ አስተያየት የሰጡት የልጃቸው የትዊተር ሰሌዳ ለጊዜው እንዲዘጋ መደረጉን ተከትሎ ነው።
በጤና ባለሞያዎች ዘንድ ሀይድሮክሲክሎሪን ኮቪድ-19ን ይዋጋል የሚል አስተማማኝ ማስረጃ እስካሁን አልተገኘም። ከዚያ ይልቅ እንዲያውም መድኃኒቱ ለልብ ህመም ስለሚዳርግ ጥንቃቄ አድርጉ የሚሉ መረጃዎች ናቸው ተጠናክረው እየወጡ ያሉት።
ለምሳሌ ባለፉት ወራት የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ባወጣው ማስጠንቀቂያ ይህ የወባ መድኃኒት ለአደገኛ የልብ ህመም ስለሚዳርግ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
ዶናልድ ትራምፕ ይህን መግለጫ በሚሰጡበት ሰዓት በበሽታው የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር አሻቅቦ ታይቷል። በ24 ሰዓት ብቻ 1ሺህ 600 ሰዎች በመላው አሜሪካ መሞታቸው በወራት ውስጥ ያልተሰማ ክፉ ዜና ነው።
ይህን ተከትሎ መድኃኒት ከተገኘ በሚል ካሜራ በመፈብረክ የሚታወቀው ኮዳክ ኩባንያ ወደ መድኃኒት ምርት የገባ ሲሆን ከመንግሥት 765 ሚሊዮን ዶላር ብድር አግኝቷል። ይህ በካሜራ ማምረት ሥራ ለዘመናት የቆየው ኮዳክ ኩባንያ ለቫይረሱ አዲስ መድኃኒት ሲገኝ ያንን ቶሎ አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ ነው ዝግጅት እያደረገ ያለው።
ሀይድሮክሲክሎሮኩዊንን ለመጀመርያ ጊዜ በዓለም ላይ ዝናና እውቅና እንዲያገኝ ያደረጉት የ74 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲሆኑ ይህም በመጋቢት ወር ነበር የሆነው። ያን ከተናገሩ ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ ትራምፕ መድኃኒቱን ራሳቸው እየወሰዱት እንደሆነ በመናገር የጋዜጠኞችን አፍ አስከፍተዋል።
አሁን ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ በዚህ መድኃኒት ዙርያ እጅግ ጥልቅ ንባብ ስለማድረጋቸውና መድኃኒቱ በሽታውን እንደሚፈውስ እንደደረሱበት ያለ ምንም ሀፍረት አብራርተዋል።
"ይህን መድኃኒት ብትወስዱት ምንም አትጎዱም። እኔ አንድ ነገር ጥሩ ነው ስል ሁላችሁም በተቃራኒው ስለምትቆሙ ነው እንጂ መድኃኒቱ ፍቱን ነው" ብለዋል።
ትራምፕ ሰኞ ማታ 'አሜሪካ ፍሮንትላይን ዶክተርስ' የሚባል አንድ የሐኪሞች ቡድን ስለ ሀይድሮክሲክሎሮኩዊን የተናገረውን ቪዲዮ አጋርተው መነጋገሪያ ሆነው ቆይተዋል።
ፌስቡክም ሆነ ትዊተር ግን ፕሬዝዳንቱ ያጋሩትን ቪዲዮ ከሰሌዳቸው አንስቶባቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ ሐሰተኛ መረጃ ነው በሚል ነው። ሆኖም ፌስቡክና ትዊተር እርምጃውን ከመውሰዳቸው በፊት ቪዲዮዉን 17 ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል።
ትዊተር እንዲያውም ይህንኑ ቪዲዮ የፕሬዝዳንቱ የበኩር ልጅ በማጋራቱ ልጁን ለ12 ሰዓታት ከትዊተር አግዶ አቆይቶታል።
በዚህ ቪዲዮ ላይ የምትታየው ዶ/ር ስቴላ ኢማኑኤል የተባለች ሴት በርካታ ስሜት የማይሰጡ ንግግሮችን ከተናገረች በኋላ ሀይድሮክሲክሎሮኩዊንን በመጠቀም 350 ሰዎችን እንደፈወሰች ስትናገር ትታያለች።
ዶናልድ ትራምፕ በምሽቱ መግለጫቸው ይህቺን ሴት ዶክተር መድኃኒቱን በማድነቋ እጅግ አድርገው አሞካሽተዋታል።
ትራምፕ ሰኞ ዕለት ከከፍተኛ የጤና አማካሪያቸው ከዶ/ር አንተኒ ፋውቺ አቋም የሚጻረሩ በርካታ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን ጋዜጠኞች ይህን ተከትሎ ከዶ/ር ፋውቺ ጋር ቅያሜ ይኖራቸው እንደሁ ፕሬዝዳንቱን ጠይቀዋቸዋል።
ትራምፕ በሰጡት ምላሽ ከዶ/ር አንተኒ ፋውቺ ጋር... | ዶናልድ ትራምፕ የወባ መድኃኒት ለኮሮናቫይረስ ፈውስ ነው አሉ | amh_Ethi | train | goodtitle | GEM/xlsum | amharic | 403 | UNK | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
End of preview. Expand
in Data Studio
README.md exists but content is empty.
- Downloads last month
- 25